ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች በታንዛንያ | ኢትዮጵያ | DW | 28.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች በታንዛንያ

የታንዛኒያ መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ግዛቱ የገቡ ኢትዮጵያዉን ስደተኞችን እያሠረ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልስ ማስጠንቀቁ በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ላይ አስጠንቅቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:48
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:48 ደቂቃ

ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች በታንዛንያባለፈዉ ሳምንት የሃገሪቱ ፖሊሶች አሸጋጋሪ ደላሎች ዳሬ ኤስ ሳላም ዉስጥ ሁለት ትናንሽ ክፍሎች ባሏት አነስተኛ ቤት ያጨቋቸዉ ከ40 በላይ ኢትዮጵያዉንን መያዛቸዉ መሰማቱ ይታወቃል። ከዚያ በፊት በርካታ ኢትዮጵያዉያን በከባድ መኪና ተጭነዉ ከታንዛኒያ ወደ ማላዊ ሊሻገሩ ሲሞክሩ በታንዛኒያ ፀጥታ አስከባሪዎች ተይዘዉ እንደነበርም ይታወሳል። የታንዛኒያ የሃገር ግዛት ሚንስትር ቻርልስ ኪትዋንጋ እንዳሉት መንግሥታቸዉ በሕገ-ወጥ መንገድ ታንዛኒያ የገቡ የዉጪ ሃገር ዜጎችን በተለይ ኢትዮጵያዉያንን ለመያዝና ወደ ሃገራቸዉ ለማጋዝ ልዩ ዘመቻ ጀምሯል። ታንዛኒያ ዉስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን በሕገ-ወጥ መንገድ ይኖራሉ ወይም ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመጓዝ ጊዜና ገንዘብ ይጠብቃሉ። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ሃገር ታንዛንያ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለሚሰደዱ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ዜጎች ዋና መሸጋጋሪያ መሆንዋ ይታወቃል። ሥለ ሕገ-ወጥ የሰዉ አዘዋዋሪዎችና ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በተመለከተ የኬንያዉን ወኪላችንን አነጋግረነዋል።

ፋሲል ግርማ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic