ኢትዮጵያዉያን ለምን ይሰደዳሉ? | ኢትዮጵያ | DW | 15.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዉያን ለምን ይሰደዳሉ?

ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘግቡ የአፍሪቃ ሃገራት አንድዋ መሆንዋ እየተነገረ ነዉ። በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከሰፈነ በርካታ ዓመታት ማስቆጠሩን የሃገሪቱ መንግሥትና ደጋፊዎቹ ይናገራሉ። ይሁንና የኤኮኖሚዉ እድገትም ሆነ ሰፈነ የተባለዉ ሰላም ለዜጎች በተለይም ለወጣቶች ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ያመጣ አይመስልም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 28:52
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
28:52 ደቂቃ

ዉይይት-አደገኛዉ የስደተኞች ጉዞ

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በገፍ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየተሰደዱ ነዉ። የተመድ እና ሌሎች የስደተኞች ጉዳይን የሚከታተሉ ዓለም አቀፍ ማኅበራት እንደሚሉት ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች ጦርነት እንዳፈረሳት ሶማልያ ወይም ከፍተኛ ጭቆና ይፈጸምባታል ተብላ እንደምትወቀሰዉ ኤርትራ ሁሉ ኢትዮጵያም በርካታ ዜጎችዋ እየተሰደዱ ነዉ። ወደ አዉሮጳ ደቡብ አፍሪቃና ሃረብ ሃገራት ለመግባት የሚሰደዱ ኢትዮጵያዉያን በየአካባቢዉ የሚደርስባቸዉ ግፍና በደል ዘግናኝ መሆኑን በህይወት የተረፉ ስደተኞች ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ በየበረሃዉና በየባህሩ ሞተዉ ይቀራሉ። ለኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በገፍ መሰደድ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ በየጊዜዉ የሚደረጉ ጥናቶች እና ዉይይቶች ቢኖሩም እስካሁን ድረስ ወጥ ስምምነት ላይ የሚያደርሱ ስምምነቶች የሉም። ወጣቶቹም መሰደዳቸዉን አላቋረጡም። በቅርቡ የሜዲተራንያን ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ሰምጠዉ ከሞቱት 500 ያህል ስደተኞች መካከል ከግማሽ የሚበልጡት ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ተብሎ ይታመናል። በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት የዛንብያ ፖሊስ 34 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ግዛቱን አቋርጠዉ ለማለፍ ሲሞክሩ ይዞ ማሰሩ ይታወቃል። ይህ በቅርቡ የሰማነዉና በምሳሌ የምንጠቅሰዉ ብቻ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ለምን ይሰደዳሉ? የዛሬዉ የምንወያይበት ርዕስ ይሆናል?

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic