ኢትዮጵያዉያንና ስነ-ግጥም ስራዎቻቸዉ | ባህል | DW | 13.09.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

ኢትዮጵያዉያንና ስነ-ግጥም ስራዎቻቸዉ

እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። በ2005 ዓ,ም የመጀመርያዉ ሳምንት የባህል ቅንብራችን የፕሮፊሰር አዱኛን የመልካም ምኞት መግለጫ ግጥም ይዞአል። በኢትዮጵያ እና በዉጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ገጣሚዎች የተሰባሰቡበት የግጥም መድብልንም በተመለከተ ከፀሃፊዎች ጋር ቆይታ አድርገናል።

እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። በ2005 ዓ,ም የመጀመርያዉ ሳምንት የባህል ቅንብራችን የፕሮፊሰር አዱኛን የመልካም ምኞት መግለጫ ግጥም ይዞአል። በኢትዮጵያ እና በዉጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ገጣሚዎች የተሰባሰቡበት የግጥም መድብልንም በተመለከተ ከፀሃፊዎች ጋር ቆይታ አድርገናል። ኢትዮጵያን ፖየትሪ በተሰኘ በፊስ ቡክ ድረ-ገጽ ላይ ከተለያዩ አለም ገራት የተሰባሰቡ አስር ኢትዮጵያዉያን ገጣሚዎች አስር በአስር የተሰኘ የግጥም መድብል አሳትመዉ ለአንባብያን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የሆኑት የድረ-ገጹ መስራች ገጣሚ ሳምሶን ተፈራ አስሩ ገጣምያን መድብላቸዉን ለአንባብያን ለማቅረብ መዲና አዲስ አበባ ላይ ለመሰባሰብ እቅድ ላይ እንደሆን አጫዉተዉናል። በጀርመን ድስልዶርፍ ከተማ ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ የሚገኙት ገጣሚ አሸናፊ ለማ ኢትዮጵያን ፖየትሪ በተሰኘዉ የማህበረሰብ መገናኛ ገጽ ላይ ግጥሞቻቸዉን ለአንባብያን ያካፍላሉ። አሁን ደግሞ አስር በአስር በተሰኘዉ የግጥም ስብስብ ላይ ተካፋይ ናቸዉ።  ሌላዉ በስዊድን ትምህርቱን ለመከታተል ከመጣ ሁለት አመት እንደሆነዉ የነገረን ወጣት አብዲ ሰይድ ግጥምን መጻፍ የጀመረዉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ እንደነበር ነግሮናል። የአስር በአስር የግጥም መድበል አባልም ነዉ። አስር ገጣምያንን ያካተተዉ የግጥም መድብል አስር በአስር የግጥም መድብል ስድስት ገጣምያንን ከኢትዮጵያ ሌሎቹ በዉጭዉ አለም የሚኖሩትን ኢትዮጵያዉያን አካቶአል። ከገጣምያኑ ጋር ዉይይት አድርገን ግጥሞቻቸዉን አካፍለዉናል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 13.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/167rO

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 13.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/167rO