ኢትዮጵያዉን በሱዳን ወከባ በዛባቸዉ | ኢትዮጵያ | DW | 24.07.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዉን በሱዳን ወከባ በዛባቸዉ

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በሱዳን መንግስት ወታደሮች የሚደርስባቸዉ ጥቃትና ወከባ እየተባባሰ መሄዱ እየተሰማ ነዉ።

ካርቱም

ካርቱም

በድንበር አቅራቢያ በገዳሪፍና ገላባት አካባቢ ለዓመታት በተለያዩ መስኮች ተሰማርተዉ ኑሮን እየገፉ ከሚገኙ ወገኖች መካከል በወታደሮች ከተደበደቡ፤ የፈላ ዉሃ ከተደፋባቸዉና፤ መሰል ጥቃት ከተፈፀመባቸዉ ሌላ በካርቱም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ይሰሩ የነበሩም እንዲሁ ከስራቸዉ በሱዳን መንግስት የሰራተኛ ጉዳይ ትዕዛዝ ተፈናቅለዋል።