ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅና የርዳታ አቅርቦቱ | ኢትዮጵያ | DW | 13.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

  ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅና የርዳታ አቅርቦቱ

የዓለም ምግብ ድርጅት WFP እንደሚለዉ ያለዉ የምግብ ክምችት ተረጂዉን ለአንድ ወር ያክል እንኳ የሚቀልብ አይፈለም።የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ለጋሽ ሐገራት ለኢትዮጵያዉን ችግረኞች እንዲረዱ ከተጠየቁት 1.13 ቢሊዮን ዶላር ዉስጥ እስካሁን የረዱት 262 ሚሊዮን ብቻ ነዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:16

  ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅና የርዳታ አቅርቦቱ

ኢትዮጵያ ዉስጥ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልገዉ ሕዝብ የሚታደል በቂ የርዳታ እሕል አለመኖሩን የዉጪ የርዳታ ድርጅቶች አስታዉቀዋል።የዓለም ምግብ ድርጅት WFP እንደሚለዉ ያለዉ የምግብ ክምችት ተረጂዉን ለአንድ ወር ያክል እንኳ የሚቀልብ አይፈለም።የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ለጋሽ ሐገራት ለኢትዮጵያዉን ችግረኞች እንዲረዱ ከተጠየቁት 1.13 ቢሊዮን ዶላር ዉስጥ እስካሁን የረዱት 262 ሚሊዮን ብቻ ነዉ።ይሁንና የኢትዮጵያ የብሔራዊ የአደጋ ሥራ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ እንደሚሉት መንግሥት ለረሐብ የተጋለጠዉን ሕዝብ ለመርዳት እየጣረ ነዉ።ኢትዮጵያ ዉስጥ ወደ ስምንት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ የምግብ ርዳታ ይፈልጋል።ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች