″ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?″ ውይይት በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 11.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

"ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?" ውይይት በአዲስ አበባ

ኢትዮጵያ የሊቢያ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል? ተቃዋሚው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ በሳምንቱ መገባደጃ ባካሔደው የውይይት መድረክ የተሳተፉ አንድ ግለሰብ ይኸ ሥጋት አድሮባቸዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በሊቢያ እና በሶማሊያ መንገድ ላለመጓዙ ማንም የሚያውቅ የለም ሲሉ ተደምጠዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:42

ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ውይይት


ኢትዮጵያ የሊቢያ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል? ተቃዋሚው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ በሳምንቱ መገባደጃ  ባካሔደው የውይይት መድረክ የተሳተፉ አንድ ግለሰብ ይኸ ሥጋት አድሮባቸዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በሊቢያ እና በሶማሊያ መንገድ ላለመጓዙ ማንም የሚያውቅ የለም ሲሉ ተደምጠዋል። "ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?" በሚል መሪ ቃል በተካሔደው ውይይት ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም እና ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጨምሮ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ዜጎች ታድመውታል። ውይይቱ ኢትዮጵያ ገጥመዋታል በተባሉ ችግሮች ላይ ተነጋግሯል። ተመሳሳይ ውይይቶች በወርኃ ታኅሳስ በተከታታይ እንደሚደረጉ ፓርቲው አስታውቋል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ 
አርያም ተክሌ 

Audios and videos on the topic