ኢትዮጵያንና ህዝቧን የጎዳው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ | ኢትዮጵያ | DW | 21.11.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያንና ህዝቧን የጎዳው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ

«ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው» እንደሚባለው ሰዎች በተሳሳተ መረጃ በጥላቻ ለበቀል ሲነሳሱ፣ለአደጋ ሲጋለጡ፣ ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ፣ ሲሸበሩ፣ሲጨነቁና ግራ ሲጋቡ ማየት የተለመደ ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ የፕሮፓጋንዳው ጦርነት፣ በጦር ግንባር ከሚካሄደው በላይ እየተፋፋመ መሄድ ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረጉ የሰላም ጥረቶች ላይም ተጽእኖ እያሳደረ ነው።

የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ጦርነት በኢትዮጵያ

ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያው ጦርነት ካደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት  ባልተናነሰ በየአቅጣጫው የሚካሄደው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሀገሪቱንና ህዝቧን ለከፋ ጉዳት ማጋለጡ ቀጥሏል። በተፈላሚ ወገኖችና በደጋፊዎቻቸው በመደበኛም ይሁን መደበኛ ባልሆኑ መገናኛ ብዙሀን ጭምሮ በተለያዩ ጉዳዮችች መነሻነት የሚሰራጩ የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎች እውነቱን ከሀሰት ለመለየት አዳጋች አድርገውታል። በሀገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ እየተደረገ የኢንተርኔት ሰራዊት አሰማርቶ በየአጋጣሚው ፍጽም መሰረት የሌለው የሀሰት መረጃ ማስተላለፍ ፣አንባቢ አድማጭ ተመልካቹ ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ እንቅፋት ሆኖ ቀጥሏል። «ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው» እንደሚባለው ሰዎች በተሳሳተ መረጃ ሰበብ በጥላቻ ለበቀል ሲነሳሱ፣ለአደጋ ሲጋለጡ፣ ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ፣ ሲሸበሩ፣ሲጨነቁና ግራ ሲጋቡ ማየት የተለመደ ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ የፕሮፓጋንዳው ጦርነት፣ በጦር ግንባር ከሚካሄደው በላይ እየተፋፋመ መሄድ ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረጉ የሰላም ጥረቶች ላይም ተጽእኖ ማሳደሩ አንደማይቀር ይገመታል።በመደበኛና በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተባባሰው የፕሮፓጋንዳ ጦርነትና የተሳሳተ መረጃ

ስርጭት የሚያደርሰው ጉዳት እንዲሁም ችግሩና መከላከያው መንገድ የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው።በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ እንግዶች ጋብዘናል። እነርሱም ዶክተር እንዳልክ ኅይለማርያም በዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ በሚገኘው አምሌን ዩኒቨርስቲ የኮምኒኬሽንና የሚድያ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰር ፣ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ UMD ሚዲያ የተባለ ድረ ገጽ ባለቤት ከካናዳ እንዲሁም በፍቃዱ ኃይሉ የሰብዓዊ መብቶች አቀንቃኝ ከአዲስ አበባ ናቸው። በዚህ ውይይት ላይ የመንግሥት ተወካዮች እንዲገኙልን ጋብዘን ነበር።ሆኖም የመንግሥት ኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት ፣ተወያይ ለመመደብ ፈቃደኛ መሆኑን ቢገልጽልንም ሳይሳካ በመቅረቱ አልተገኙልንም።ሙሉውን ውይይት ለመከታተል ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ

ኂሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic