ኢትዮጵያና የጀርመናዊዉ ጋዜጠኛ ትዉስታ | አፍሪቃ | DW | 16.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኢትዮጵያና የጀርመናዊዉ ጋዜጠኛ ትዉስታ

የመረጃዉን ትክክለኛነት ለማጣራት ግን ሔደማን እንደታዘበዉ ሲበዛ ከባድ ነዉ።በኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰዉ ጭቆናና ወከባ ደግሞ ከፍተኛ በመሆኑ መረጃ ማግኘቱም፥ ማጣራቱም ካአደጋ ላይ የሚጥል ነዉ።

--- DW-Grafik: Per Sander 2010_11_24_symbolbild_pressefreiheit.psd

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወረ ከሰወስት ዓመታት በላይ የዘገበዉ ጀርመናዊ ጋዜጠኛ ፊሊፕ ሔደማን ልምዱንና ገጠመኙን የተረከበትን መፅሐፍ በቅርቡ «በሞት የሚያፈዘዉ ሰዉዬ» በሚል ርዕሥ አሳትሟል።ለጀርመንና ለሲዊስ ታዋቂ ጋዜጦች ከኢትዮጵያ ሲዘግብ የነበረዉ ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ ለዉጪ ጋዜጠኞች መረጃ ማግኘቱ አይገድም ይላል።የመረጃዉን ትክክለኛነት ለማጣራት ግን ሔደማን እንደታዘበዉ ሲበዛ ከባድ ነዉ።በኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰዉ ጭቆናና ወከባ ደግሞ ከፍተኛ በመሆኑ መረጃ ማግኘቱም፥ ማጣራቱም ካአደጋ ላይ የሚጥል ነዉ።ጋዜጠኛና ደራሲ ሔደማንን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ