ኢትዮጵያና የአዲሱ ዓመት ተስፋ | እንወያይ | DW | 13.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

እንወያይ

ኢትዮጵያና የአዲሱ ዓመት ተስፋ

እንኳን ለ 2008 ዓ,ም በሰላም አደረሳችሁ ትናንት የተሰናበትነዉ አሮጌ ዓመት 2007 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በአሸባሪዉ «IS» ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት፤ በደቡብ አፍሪቃ በእሳት ተቃጥለዉ ህይወት የጠፋበት፤ በየመን የርስ በርስ ጦርነት አጣብቂኝ ዉስጥ የገቡበት ነበር። 2007 ዓ,ም የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የተካሄደበትና ገዥዉ የኢሕአዴግ ፓርቲ 100 በ 100 ያሸነፈበት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃነት አጣን እያሉ ወቀሳ ያሰሙበት፤ የልዕለ ኃያልዋ ሃገር የዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የጎበኙበት ፤ ኑሮ የተወደደበትና፤ የዋጋ ግሽበት የታየበት ነዉ። ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች በተለያዩ የዓለም የስፖርት ዉድድሮች ድል ያስመዘገቡበትም ነበር። አዲስ አበባ ቀላል የባቡር መሥመር የተዘረጋበት፤ ታሰረዉ የነበሩ አንዳንድ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ድንገት የተለቀቁበት፤ ፍርድ ቤት በተሰጠ ቀጠሮ ዳኖች ሳይገኙ ቀርተዉ ዳግም ሌላ ቀጠሮ የተሰጠበት ዓመትም ነዉ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ እስራት የተበየነባቸዉም በዚህ ዓመት ነዉ። የደቡብ ሱዳናዉያን ተቀናቃኝ ኃይሎች ሽምግልና የተስተናገዱበት፤ ኤሌኞ የተሰኘ አዙሪት የአየር ለዉጥ፤ በኢትዮጵያ ድርቅ ያስከተለበትና የምግብ ርዳታ ያስፈለገበት ዓመት ነበር። እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ በኢትዮጵያ ትናንት በሸኘነዉ ዓመት የታዩ ክስተቶች ናቸዉ።

ኢትዮጵያና የአዲሱ ዓመት ተስፋ የዛሬ እንወያይ ርዕስ ነዉ። በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩልን ሶስት እንግዶችን ጋብዘናል።ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን እንዲያደምጡ እንጋብዛለን

Audios and videos on the topic