ኢትዮጵያና የአዉሮጳ ሕብረት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ኢትዮጵያና የአዉሮጳ ሕብረት

አምባሳደሯ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያን የፓለቲካ የሠብአዊ መብትና የዴሞክራሲ ይዞታን፤ የእስረኞች ሁኔታን የሚመለከት እንደነበር የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል

በኢትዮጵያ የአዉሮጳ ሕብረት አምባሳደር ወይዘሮ ቻንታል ሒብሪክት ሰሞኑን ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር በየተራ ተወያይተዋል።አምባሳደሯ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያን የፓለቲካ የሠብአዊ መብትና የዴሞክራሲ ይዞታን፤ የእስረኞች ሁኔታን የሚመለከት እንደነበር የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል።የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ቢሮ ዋና ቃል አቀባይ ማይክ ማን ግን ዉይይቱን ሁል ጊዜ የሚደረግ በማለት ገልፀዉታል።ቃል አቀባዩ በዉይይቱ የተነሱትን ዝርዝር ጉዳዮች መግለፅም አልፈለጉም።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ቃል አቀባይ ማንን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic