ኢትዮጵያና የተመድ | ኢትዮጵያ | DW | 28.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያና የተመድ

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ተለወጭ አባል እንድትሆን የአፍርቃ መሪዎች ባለፈዉ ጥር ባደረጉት ጉባኤ ብቸኛ እጩ አድርገዉ መወከላቸዉ ይታወሳል። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ በተለያዩ መድረኮች ለአባልነት ለመመረጥ ሰፊ ዘመቻ ስታካሒድ መቆየቷም ዘገባዎች ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:26

ኢትዮጵያና ተመድ

ዛሬ ኒዉዮርክ ዉስጥ የሚሰየመዉ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ኢትዮጵያን አባልነት አፅድቋል። የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃልአቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ለዓለምአቀፉ ህብረተሰብ የበለጠ አገልግሎት ታበረክታለች ይላሉ።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ እና ዲሞክራሳዊ መብቶች ይጥሳል በሚል የመብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ እየወቀሱት ነዉ። ኢትዮጵያ እንደዚህ ዓይነት ስም ይዛ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ምክር ቤት አባል እንዴት መሆን ትችላለች፣ ከተመረጠችም በአፍሪቃ ያለዉን የፍትህ፤ የነፃነት እና የዲሞክራሲ መብቶችን እንዴት ታስጠብቃለች ብሎ የሚተቹም አልጠፉም። አቶ ተወልደ ግን አገሪቱ <<ዴሞክራስን ለማስፈን የምታደርገዉን ጥረት>> ሌላ አፍሪቃ ማህበረሰብ እንደሚጠቅም ጠቅሰው የዲሞክራሲን ባሕል እያሳደግን ነዉ ሲሉም ጠቅሰዋል።


ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ተለወጭ አባልነቷ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ዉስጥ በአፍሪቃ ትልቅ ሚና እንደምኖራትም አብራርተዋል። እንደ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ማብራሪያ ኢትዮጵያ ከተመረጠች የአፍሪቃ ጉዳዮችን አጉልታ እንምታወጣ እናም ለአፍሪቃ <<ህዝቦች መብት እና ጥቅም መከበር>> ከአለማቀፉ ማሕበረሰብ ጋር አብራ እንደምትሰራም ጠቅሰዋል።

በዝህ ጉዳይ ላይ በዶቼ ቬሌ ደህረ ገፅ ላይ እንድወያዩ አድርገን ነበር። አብዛኛዉ አስተያየት ሰጭዎች አፍሪቃ ዉስጥ የትኛዉም አገር ሰብዓዊም ሆነ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እንደማያከበር ጠቅሶ ኢትዮጵያም ብትመረጥም <<ወንበር ላይ ከመቀመጥ ሌላ ምንም አይነት ለዉጥ>> አታመጣም ሲሉ ይተቻሉ። ሌሎች ደግሞ <<እንኳን ተለዋጭ አባልነት አይደለም የዋና ጸሐፊውን ወንበር ቢሰጣትም ለማህበረሰቡ የምትጨምርለት ነገር የለም>> ካሉ በዋላ የምዕራባዊያኑን ፍላጎት ከማስጠበቅ ዉጭ ለዉጥ አታመጣም በማለት አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic