ኢትዮጵያና አሥጊው የምድር ነውጥ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 27.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ኢትዮጵያና አሥጊው የምድር ነውጥ፣

ጥር 4 ቀን 2002 ዓ ም፣ በካራይብ ባህር የምትገኘውን ሀገር ሄይቲን ፣ በሪኽሽር መለኪያ 7.0 የደረሰ የምድር ነውጥ ለ 35 ሴኮንድ ክፉኛ አርገፍግፎ ፣ በተለይ 3,5 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባትን መዲናይቱን ፖርት ኦ ፕራንስን ባድማ ነው ያስመሰላት።

default

የምድር ነውጥ የሚያስከትለው ጥፋት፣

የአገሪቱ መንግሥት በሰጠው መግለጫ መሠረት 150,000 ያህል ህዝብ ህይወቱን ሲያጣ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ቆስለዋል። አደጋው ከደረሰ ከ አንድና 2 ሳምንታት በኋላም ቢሆን ተዓምር ባሰኘ ሁኔታ አንዳንድ ሰዎች ከህንጻዎች ፍርስራሽ ሥር ሊገኙ ችለዋል። በሄይቲ የደረሰው ዓይነት አደጋ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አገሮች አጋጥሟል ወደፊትም ማጋጠሙ አይቀርም።

የምድር ነውጥ ከሚያሠጋቸው አገሮች አንድዋ ኢትዮጵያ መሆንዋ እሙን ነው። የምድር ነውጥን መግታት የሚያስችል አንዳች ብልሃት የለም። አያድርስ እንጂ ቢያጋጥም ግን ፣የጥፋቱን መጠን በእጅጉ ለመቀነስ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ ይቻላል፣ ተገቢም ነው። ኢትዮጵያውያን ከሄይቲው ድቀት ማግሥት ምን ዓይነት መልእክት ሊቀስሙ ይችላሉ? በሚለው ነጥብ ዙሪያ ይበልጥ ከማትኮራችን በፊት፣ በመጀመሪያ ምድርን የሚያንቀጠቅጣት የሚንጣትም ሆነ የሚያርገፈግፋት ኃይል ምን እንደሆነ ግንዛቤው ይኖረን ዘንድ እንዲያብራሩልን ፣ ለዛሬ ፣ በሳን ዲዬጎ፣ ካሊፎርኒያ ፣ ዩናይትድ እስቴትስ የሚገኙ አንድ ባለሙያ አነጋግረናል።

እርሳቸውም ፣ አሁን በሳን ዲየጎ የኒቨርስቲ የኢንጀኔሪንግ ፕሮፌሰር የሆኑት፣ በዚሁ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴ ናቸው። ቀደም ሲል ዶ/ር ሳሙኤል፣ ከህንጻ ምህንድስናና ከምድር ነውጥ ምርምር ጋር በተያያዘ ኢንጂኔሪንግ ላይ ባተኮረው RAM ኢንተርናሽናል በተሰኘው ኩባንያ ውስጥ የአንድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለዓመታት ከመሥራታቸውም፣ ከሚያተኩሩበት የምርምር ዘርፍ ሌላ፣ የምድርን አርገፍጋፊ ኃይል ያገናዘበው የኢትዮጵያ የኢንጀሪንግ የምክክር ኮሚቴ ባልደረባ ናቸው። ዶ/ር ሳሙኤል ስለምድር ነውጥ ምንነት እንዲህ ይላሉ።

(ድምፅ)--------

ተክሌ የኋላ