ኢትዮጵያና ስዊድን፤ | ኢትዮጵያ | DW | 13.08.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያና ስዊድን፤

ኢትዮዽያ በሲውዲን ያለውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን ጠቃላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከትላንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

default

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ፤ ለኢትዮጵያ ፣ ከስዊድን ይልቅ በብራዚል ኤምባሲ መክፈት እንደሚሻላት ተናግረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኤምባሲው ተልዕኮውን ሊወጣ ባለመቻሉ መዘጋቱንና ከዚያ ይልቅ በብራዚል መክፈት እንደሚሻል ገልጸዋል። የሲውዲን መንግስት ይህ የኢትዮዽያ መብት ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል። በሲውዲን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አንድሬ ዮርሌ ለዶቸ ቬሌ እንደገለጹት ኢትዮዽያ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችበትን ምክንያት እንደማያውቁ ሀገራቸው በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የምትሰጥበት ምክንያት አንደሌላት ተናግረዋል። ኢትዮዽያ ይህን እርምጃ ብትወስድም ሲውዲን በአዲ አበባ ያለውን ኤምባሲዋን እንደማትዘጋው ኃላፊው አንድሬ ዮርሌ ገልጸዋል።v

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic