ኢትዮዽያ--የኃይል ሽያጭ ለጎረቤት ሀገራት | ኢትዮጵያ | DW | 09.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮዽያ--የኃይል ሽያጭ ለጎረቤት ሀገራት

ወደሱዳን የመስመር ዝርጋታው ተጠናቋል። የጅቡቲው እስከመጪው ጥቅምት ወር ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። መንግስት ቅድሚያ ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ነው ይላል።

default

ኢትዮዽያ ለሱዳን በመጪው ጥቅምት ወር ኃይል ልትሸጥ ዕቅድ እንዳላት አስታወቃለች።

ለሱዳን ለጅቡቲና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ ቀደም ብላ ስምምነት ማድረጓ ይታወሳል። በዚሁ መነሻነት ከመጪው ጥቅምት ወር ጀምሮ ሽያጭ ሊኖር እንደሚችል የኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን አስታውቋል። ኮርፖሬሽኑ የኃይል ሽያጩ ተግባራዊ የሚሆነው የሀገር ውስጡ ፍላጎት ከተሟላ በኃላ እንደሆነም ገልጿል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ምህረት ደበበ በተለይ ለዶቸ ቤሌ እንደገለጹት እስከመጪው ጥቅምት ወር ድረስ ወደጅቡቲና ሱዳን የሚዘረጋው የመስመር ግንባታ ይጠናቀቃል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic