ኢትዪጽያ ቋንቋዎች እና ጥበቃዉ | ባህል | DW | 14.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ኢትዪጽያ ቋንቋዎች እና ጥበቃዉ

ቋንቋ የአንድ ህብረተሰብ ባህል እዉቀት እና ፍላጎት አጠቃሎ የያዘ፣ የአንድ ህብረተሰብ ምንነት መግለጫ ነዉ። ቋንቋ ሞተ ስንል ምን ማለታችን ነዉ?በአገራችን ስንት ቋንቋዎች ይነገራሉ? በሞት ላይ ያሉ አልያም የሞቱ ቋንቋዎችስ ስንት ናቸዉ?

default

የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ተቋም UNESCO እዚህ በቦን ከተማ ያለዉ ቅርንጫፍ በአለማችን ዙርያ ሚነገሩ 6000 ያህል ቋንቋዎች መካከል ግማሱ እንዳይጠፋ ያሰጋል የሚል መግለጫ ከሁለት ሳምንት በፊት ማዉጣቱ የሚታወስ ነዉ። ይህንን ጥናት UNESCO ያወጣዉ የካቲት 14 ቀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊዉን የእናት ቋንቋ ወይም የአፍመፍቻ ቀን ለመጠበቅ ሲባል የተወሰነዉን ቀን አስቦ የዋለ እለት ነበር። በቦን ከተማ UNESCO ቢሮ በጉዳዩ ዙርያ ባለሞያ አግኝተን በምእራባዉያኑ አገራት በተለይም በጀርመን ያሉ አራት ያህል ቋንቋዎች በመሞት ላይ መሆናቸዉን እንዳጫወቱን የሚታወስ ነዉ። በዛሪዉ እለት ጥንቅራችን በአገራችን ስንት ቋንቋዎች ይነገራሉ? በሞት ላይ ያሉ አልያም የሞቱ ቋንቋዎችስ ስንት ናቸዉ? ስንል ባለሞያ አነጋግረን የዛሪዉን ጥንቅር ይዘናል

አዜብ ታደሰ