1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢስታንቡል የሃይማኖት መሪዎች ማሳሰቢያ

ሰኞ፣ ኅዳር 22 2007

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን አንድነት ፓትሪያርክ በርጦሎሜዎስ ቀዳማዊ ፣ ክርስቲያኖች ከመካከለኛው ምሥራቅ እንዲጠፉ የመላው ዓለም ፍላጎት አይደለም አሉ።

https://p.dw.com/p/1Dxpc
Papst Franziskus in Istanbul 30.11.2014
ምስል Reuters/U.Bektas

ሁለቱ ታዋቂ የሃይማኖችት መሪዎች፤ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ ክርስቲያኖች በአስጨናቂ ሁኔታ ላይ ሆነው ለሚያቀርቡት ጥሪ፣ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የሚመጥን ምላሽ እንዲሰጣቸው ይሻሉ ብለዋል።

Papst Franziskus in Istanbul 30.11.2014
ምስል Reuters/U.Bektas

የካቶሊካዊቷ ቤተ ክርስቲያን ርእስ፤ ፍርንሲስ፤ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሪቸፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በተወያዩበት ወቅት፤ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የሙስሊሞች፤ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ምሁራን፣ በእስልምና ስም የሚወሰድ የኃይል ርምጃን በግልጽ ቢያወግዙ ማለፊያ ነበረ ማለታቸውም ተጠቅሷል። ፍራንሲስ ፤ «ሙስሊሞች ሁሉ አሸባሪዎች ናቸው »የሚሉ ወገኖችን ትክክል አይደሉም ሲሉ በጥብቅ ወቅሰዋል ። ክርስቲያኖች ሁሉ አክራሪዎች ናቸው ብሎ መደምደም እንደማይቻል ሁሉ ሙስሊሞ ች ሁሉ አሸባሪዎች ናቸው ማለት ፍጹም ስህተት ነው።

Papst Franziskus in Istanbul 30.11.2014
ምስል Reuters/O.Orsal

አርጀንቲናዊው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፤ በአሁኑ ጊዜ በመካከለኛው ምሥራቅ ተዛመተ ያሉትን ክርስቲያኖችን መፍራትና መጥላት፤ ተገቢ ያልሆነ ርምጃ በማለት አውግዘዋል። ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱ አክራሪ ሙስሊሞችንም ከሰዋል። ፍራንሲስ ፣ የአገሮችን ስም ባይጠቅሱም የተወሰኑ ባለሥልጣኖች፤ በእነዚያው አገሮች አንድም ክርስቲያን እንዳይኖር ፣ ከእነአካቴው ነቅሎ እንዲወጣ ያደርጋሉ ማለታቸው ተጠቅሷል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስና የኦርቶዶካሳውያኑ ፓትሪያርክ በርጦሎሜዎስ ቀዳማዊ፣ ትናንት በጋራ የሐዋርያውን ቅዱስ እንድርያስ ዕለተ ሞት በልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት አስበዋል። ሁለቱ መንፈሳዊ መሪዎች ስለአብያተ-ክርስቲያን እርቅና አንድነት መነጋገራቸውም ተወስቷል።

ፍራንሲስ፣ እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል።«በመንፈስ ቅዱስ ከተመራንና ከሠራን የዓይነት ብዛትና ልዩነት ፈጽሞ አያወዛግብንም። መንፈስ ቅዱስም፤ ዓይነቱን ፣ በቤተክርስቲያን ጉባዔ እንድናኖረው ይገፋፋናል። »

ተክሌ የኋላ

ልደት አበበ