ኢሰመጉ ረቂቅ የህትመት ውልን መቃወሙ | ኢትዮጵያ | DW | 21.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢሰመጉ ረቂቅ የህትመት ውልን መቃወሙ

የውል ረቂቁን የኢትዮጵያ የግል ፕሬስ አሳታሚዎች በህገ መንግሥቱ ገደብ እንዳይጣልበት በተደነገገው የመናገር ነፃነት ላይ በህትመት ውል ኮንትራት ስም የተጣለ ቅድሚያ ምርመራ ነው ሲሉ ዓለም ዓቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትም እያወገዙት ነው ።

***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B


በቅርብ ጊዜ በማተሚያ ቤቶች ተዘጋጅቶ የቀረበው የውል ረቂቅ የህገ መንግሥቱን አንቀፅ የሚጥስ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ ። ኢሰመጉ የፕሬስ ነፃነት ይከበር በሚል ዛሬ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ሁኔታውን መርምሮ መፍትሄ እንዲስጠም ጠይቋል ። ውሉን የኢትዮጵያ የግል ፕሬስ አሳታሚዎች በህገ መንግሥቱ ገደብ እንዳይጣልበት በተደነገገው የመናገር ነፃነት ላይ በህትመት ውል ኮንትራት ስም የተጣለ ቅድሚያ ምርመራ ነው ሲሉ ዓለም ዓቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትም እያወገዙት ነው ። የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በበኩሉ የህትመት ሥራ ደረጃ ያለው ውል ሥራን በጥራት ለመስራት ታስቦ እንጂ ቅድሚያ ምርመራ አይደለም ሲል ለዶቼቬለ መልስ ሰጥቷል ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 21.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14zWj
 • ቀን 21.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14zWj