ኢራን የተነሳላትን ማዕቀብ ፕሬዚዳንቷ አወደሱ | ዓለም | DW | 17.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ኢራን የተነሳላትን ማዕቀብ ፕሬዚዳንቷ አወደሱ

ከዚህም በተጨማሪ በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ በተነሳ ማግስት እስረኞች እየተፈቱ ነው። በኢራን ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ በመተላለፍ ተከሰው በአሜሪካን እስር ቤት የነበሩ ሰባት ሰዎች ትናንት መፈታታቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

ከሰባቱ መካከል ስድስቱ የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ ድርብ ዜግነት ያላቸው ናቸው። የሁለቱ አገራት በደረሱት ስምምነት መሰረት በኢራን በእስር ላይ የነበሩ አራት ሰዎች መፈታታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኑክሌር ኃይል ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የኢራን የኑክሌር መርኃ-ግብር ከተቀመጠው ውል ጋር የተስማማ መሆኑን የሚገልጥ ዘገባ ትናንት በማውጣቱ በአገሪቱ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት የጣሉትን ማዕቀብ ቅዳሜ ዕለት አንስተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤የአውሮጳ ህብረት እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የጣሉት ማዕቀብ በመነሳቱ ኢራን የታገደባት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ማንቀሳቀስ ይፈቀድላታል። ምዕራባውያን ኩባንያዎች 80 ሚሊዮን ህዝብ ባላት ኢራን መሥራት የሚፈቀድላቸው ሲሆን አገሪቱ ድፍድፍ የነዳጅ ዘይትን ከአምስት አመታት በኋላ ለዓለም ገበያ ታቀርባለች። ኢራንና አምስት ሲደመር አንድ የሚባሉት ብሪታንያ፤ቻይና፤ፈረንሳይ፤ሩስያ እና ዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁም ጀርመን በኑክሌር መርኃ-ግብር ላይ ከስምምነት ባለፈው ሐምሌ ወር የደረሱት ዓመታት ከወሰደ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በኋላ ነበር። ውሉም ኢራን የጀመረችዉን የኑክሌር መርኃ-ግብር የኑክሌር ቦንብ ለመገንባት ሳይሆን ለሲቪል አገልግሎት ብቻ እንድትጠቀም የሚፈቅድ ነበር።

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ