ኢራንና ምዕራቡ ዓለም ዉዝግብ | ዓለም | DW | 30.12.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ኢራንና ምዕራቡ ዓለም ዉዝግብ

ኢራን በኒኩሊየር መርሃግብሯ መግፋቷንና የኒኩሊየር ጦር መሳሪያ ለመታጠቅም ዝግጅቷን ማጣደፏን አለም አቀፉ የአቶም ኃይል ተቆጣጣሪ ተቋም IAEA አመልክቷል።

የቴህራንን ምስጢራዊ አካሄድ በስጋትና በጥንቃቄ የሚከታተለዉ ምዕራቡ ዓለም አገሪቱ የተባለዉን መሳሪያ መገንባቷን ካላቆመች ተጨማሪ ማዕቀብ ሊጥልባት እንደሚችል አስታዉቋል። የአዉሮጳዉ ኅብረት አዲሱ የጎርጎሮሳዊዉ 2012ዓ,ም የመጀመሪያ ወር ማለቂያ ላይ ይህንኑ ለመወሰን እንደሚነጋገር ቀጠሮ መያዙን የኅብረቱ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ካትሪን አሽተን ቃል አቀባይ ይፋ አድርገዋል። ወደአዉሮፓ ኅብረት አገሮች ከኢራን ሌላ ሩሲያ፤ ኖርዌይ፤ ሊቢያና ስዑድ አረቢያ ነዳጅ ይልካሉ። ኢራን ፍጥጫዉን ከማርገብ ይልቅ እየገፋችበት በመሄድ ከመካከለኛዉ ምስራቅ ነዳጅ የሚሸጋገርበትን በኢራንና ኦማን መካከል የሚገኘዉን የባህር ወሽመጥ ለመዝጋት መዘጋጀቷን ተናግራለች። ያ ደግሞ ጉዳዩ ይበልጥ እንዲከር ምክንያት መሆኑ ነዉ የሚታየዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን እዘጋዋለሁ ያለችዉን አካባቢ ግፋ ቢል በሁለት ቀን ነፃ አደርገዋለሁ ባይ ናት። የምዕራቡ ዓለምና የኢራንን ፍጥጫ በሚመለከት የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤን በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic