ኢራቅ፤ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማስጠንቀቅያ | ዓለም | DW | 15.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ኢራቅ፤ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማስጠንቀቅያ

የኢራቁን ቀዉስ አስመልክቶ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር፤ በአካባቢዉ ላይ ያሉት ሀገራት ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ጠይቀዋል።

ሽታይን ማየር «ቬልት አም ዞንታግ» ለተሰኘዉ የእሁድ ሳምንታዊ ጋዜጣ ዛሬ እንደገለፁት የኢራቅ የጎረቤት ሃገራት በሃገሪቱ መልሶ ሰላም እንዲሰፍን ኃላፊነት እንዲወስዱ ጠይቀዋል።እንደ ሚኒስትሩ በአካባቢዉ ያሉት ሀገራት በሚያደርጉት የስልጣን ሽኩቻ ኢራቅ ምድር ላይም ጦርነት መከሰት የለበትም።

በተያያዘ ዜና ኢራቃዉያን ሀገሪቱን ለመቆጣጠር በጥረት ላይ ያሉትን አማፅያንን ለመዉጋት በአንድነት እንዲቆሙ ዩኤስ አሜሪካ ጥሪ አቀረበች። የዩኤስ አሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ፤ ከኢራቁ አቻቸዉ ሆሽጃር ሻቢር ጋር ባደረጉት የስልክ ዉይይት ሀገሪቱ በአንድነት መቆም አለባት ሲሉ አሳስበዋል። የዩኤስ አሜሪካ ድጋፍ ፍሬ የሚኖረዉ በኢራቅ የሚገኙ የተለያዩ ቡድኖች ልዩነታቸዉን አስወግደዉ በአንድነት ሲቆሙ፤ እስላማዊዉ አሸባሪ ቡድን ሊታገድ እንደሚችል ዋሽንግተን የሚገኘዉ የሚኒስቴር መስርያ ቤት አስታዉቋል።

ትናንት ቅዳሜ አንድ የዩኤስ አሜሪካ የአዉሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በፋርስ ባህረ ሰላጤ ላይ መድረሱም ተመልክቷል። በሌላ ዜና ባግዳድ ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰዉ ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸዉንና 23 የሚሆኑ ደግሞ ጉዳት እንደረሰባቸዉ፤ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። እንደ ሚኒስቴሩ በከተማው በሚገኝ መንገድ ላይ ፈንጅ ተቀብሮ ነበር። ጥቃቱን በማድረስ የሚጠረጠሩት የሱኒ አማፅያን ናቸው። አማፂው ቡድን ካለፉት ቀናት አንስቶ በርካታ የኢራቅ ከተሞችን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ወደ መዲና ባግዳድ ማምራቱ ይታወቃል።

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ