ኢሕአዴግና ተቃዋሚች አደራዳሪ ሊመርጡ ነው | ኢትዮጵያ | DW | 10.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢሕአዴግና ተቃዋሚች አደራዳሪ ሊመርጡ ነው

የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ እና በድርድሩ ለመቀጠል የተስማሙት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር በስምንት ዙር ካደረጉት ውይይት በኋላ አደራዳሪ ለመምረጥ ተስማሙ።ሚያዝያ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ድርድሩ የሚገዛበትን የሕግ ማዕቀፍ ይፈርማሉ። ዛሬ በተካሔደው ውይይት ያልተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው ተሰምቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:07

ድርድሩ

በስምንት ዙር ስለ ድርድር ሲወያዩ የከረሙት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ገዢው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር በመጪው ረቡዕ የሕግ ማዕቀፍ ሊፈርሙ ነው። ድርድሩ በገለልተኛ ወገን ሊመራ ይገባል የሚል አቋም ከነበራቸው ስድስት ፓርቲዎች ኃሳባቸውን የቀየሩ መኖራቸው ተሰምቷል። በድርድሩ ሒደት ላይ ልዩነታችንን አስመዝግበናል የሚሉት የመኢአድ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙሉጌታ አበበ ታዛቢዎች እንዲገኙ መስማማታቸውን ተናግረዋል።

በዛሬው ውይይት መድረክ፤መአሕድ ሰማያዊ ፓርቲ አልተገኙም። ሚያዝያ 11/2009 ዓ.ም.   'የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር ሥነ-ሥርዓት ደንብ' የተሰኘውን ዶሴ ለመፈረም ከተዘጋጁት መካከል አንዱ የሆኑት የአንድነት ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ትዕግስቱ አወሉ ናቸው ።

ድርድሩ ከመጀመሩ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ በሚደረገው ውይይት የሥነ-ሥርዓት ደንብ ለመፈረም፤ አደራዳሪ ለመምረጥ እና አጀንዳ ለመለየት መታቀዱን የተናገሩት አቶ ሙሉጌታ አበበ በድርድሩ «የምንፈልገውን ያክል ለውጥ ይመጣል ብለን አናምንም ሲሉ» ከወዲሁ ሥጋታቸውን ይገልጣሉ።

አቶ ሙሉጌታ አበበ በድርድሩ «አፋኝ ሕጎች እንዲሰረዙ» ኃሳብን እናቀርባለን ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ትዕግስቱ አወሉ በበኩላቸው ሕገ-መንግስቱ ጭምር እንዲሻሻል እንሻለን ባይ ናቸው።

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች