ኢሕአዲግ በሩብ ምዕተ ዓመት | ኢትዮጵያ | DW | 24.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢሕአዲግ በሩብ ምዕተ ዓመት

ኢሕአዲግ ማስወገዱን ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና እና በሌሎች የልማት መስኮች አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቡን በተደጋጋሚ ይናገራል። ሥልጣን የያዘበት ግንቦት 20ም በአገርቱ > ሆኗል በማለትም ይከራከራል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:30
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:30 ደቂቃ

ኢሕአዲግ

ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፤ የመብት ተሟጋቾች፤ የናፃዉ ፕረስ ባልደረቦች ግን ይሕን አይቀበሉትም።እነሱ እንደሚሉት በነዚሕ 25 ዓመታት ዉስጥ በአገርቱ ሰላም እና ዴሞካራስን በማስፈን፤ ሰብአዊ መብት በማስከበር እና ኢኮኖሚን በማሳደጉ ረገድ ኢሕአዴግ ያመጣዉ ለውጥ የለም። ነውጥ እንጅ ብሎም የሚተቹም አሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ከጠየቅናቸዉ አንዱ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ አታክልቲ ገብረእግዚአብሔር ናቸዉ።እሳቸዉ ኢሕአዲግ ባለፉት 25 ዓመታት ካከናወናቸዉ ዉስጥeዝቡ በሰላም ወቶ በሰላም እንድ ገባ አድርጎታል ስሉ አስተያየታቸዉን ያቀርባሉ።

ይሑንና ተቃዋሚዎች፤ የዉጪና የሐገር ዉስጥ የመብት ተሟጋቾች፤ ጋዜጠኞም ጭምር ኢሕአዲግ በእኮኖሚዉ ረገድ መጠነኛ ለዉጥ ቢያሳይም በሰብአዊ እና ዴሞክራሳዊ መብቶች ረገጣ ከበፊቱ ስርዓት ብዙም የተለየ አይለም ባዮች ናቸዉ። አቶ አትክልቲ ግን እየተሰሩ ያሉት የደሞክራሲ ስራዎች ጥሩ ነዉ ካሉ በዋላ ሌሎች በዝህብ አቋማቸዉ ላይሰማሙ ይችላሉም ሲሉ አስተያየታቸዉ ይሰነዝራሉ።

Regierungspartei bei Wahlen in Äthiopien vorn

ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአዲስ አበባ ነዋሪ በአፅናፋዊ ትስስር ወይም ግሎባላይዘሸን በአፅናፋዊ ትስስር ወይም ግሎባላይዘሸን ዘመን ለዉጥ አይቀሬ ስለሆነ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ እና ኮሙኒከሸን ለመጡት ለዉጦች ኢሕአዲግ ብዙም ሚና እንደሌለዉ ይናገራሉ። በፖለትካም ቢሆን አንድ ብሄር ወይም አንድ ክልል ዉስጥ ያሉት ህብረተሰቦች ኢሕአዲግ መተማመን እንዲያጡ አድርጓል ስሉ እኝሕ ግለሰብ አስተያየታቸዉን ይሰነዝራሉ።

በዶቼ ቬሌ ደህረ ገፅ ይኽን ጉዳይ በተመለከተ አወያይተን ነበር። አብዛኞቹ አስተያየት ሰጭዎች ልማትን በተመለከተ ኢሕአዲግ 25 ዓመታት ዉስጥ 85 በመቶ በሃሰት ላይ የተመሠረተ ድርጊትና ዘገበ እንደነበር እናም ያስመዘገበዉ የኢኮኖሚ ዕድገት እራሱ ያመጠዉ ሳይሆን የአለም ኢኮኖሚ የፈጠረለትን እድል እየተጎተተ ዛሬ እዚህ ደርስዋል ሲሉ ትችታቸዉን ያቀርባሉ። በፖለትካዉም ቢሆን የኢሕአዲግን ስረዓት የሚቃወሙትን ማሰር፣ ማሳደድ እና መግዳል መለያዉ ነዉ ሲሉ ይወቅሳሉ።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሓመድ

Audios and videos on the topic