ኡሁሩ ኬንያታ 100 ቀናት በስልጣን | አፍሪቃ | DW | 20.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኡሁሩ ኬንያታ 100 ቀናት በስልጣን

ባለፈዉ የካቲት ኬንያ ዉስጥ በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ቃለ-መሃላ ፈፅመዉ የፕሪዝዳንትነቱን ሥልጣን ከያዙ በኋላ አዲስን ካቢኔ ሾመዋል። ኬንያታ የሾምዋቸዉ ባለስልጣናት በአብዛኞቹ ከአሁን ቀደም በኬንያ የፖለቲካ መድረክ እንብዛም ያልተሳተፉ መሆናቸም ተነግሮአል። ይህ የኬንያታ አዲስ ጅማሮ ኬንያዉያን አዲስ ተስፋን አሰንቆላቸዋል።

እንዲያም ሆኖ ለአራተኛዉ የኬንያ ፕሪዝደንት ነገር ቀሎ አልጠበቃቸዉም። ባለፉት ቀናት እና ሳምንታት በአገሪቷ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች የደማወዝ ጭማሪ እና የተሻለ አስተማማኝ ጤና ጥበቃ እንዲኖር በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸዉ ኬንያታ የፍርድ ሂደቱ ገና አልተቋጨም። የዶቼ ቬለዉ ፊሊፕ ሳንደር ስለ ኬንያዉ ፕሪዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የ100 ቀናትን የስልጣን ግዜ እንዲህ ያስቃኘኛል። ኡሁሩ ኬንያታ ስልጣንን ሲረከቡ ሌሎች አዲስ ተመራጭ ፕሪዝዳንቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ በርካታ አዲስ ነገሮችን ለማድረግ ቃል በመግባት ነበር።

« የኛ ዓላማ አገራችንን በመካከለኛ የኢኮነሚ ደረጃ ላይ እንድትደርስ በመገንባት ሁሉም የአገሪቷ ዜጎች የከፍተኛ ደረጃ የአኗኗርን ዘዴን እንዲያጣጥም ነዉ»ከዚህ በተጨማሪ ኬንያታ በአገሪቷ ያለዉን የህክምና መስጫ አገልግሎት እንደሚያሻሽሉ ቃል ገብተዉነበር ፤ ቃላቸዉን በከፊል ፈጽመዋል። ይኸዉም በሀገሪቷ የሚገኙ ነፍሰ ጡር ሴቶች በሙሉ፤ ከሰኔ ወር ጀምሮ፤ የነጻ ህክምና ክትትል እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ግን ህብረተሰቡ ይህን መሻሻል በጥርጣሪ ነዉ የሚመለከተዉ። ምክንያቱም መንግስት እስካሁን የህክምና ባለሞያዎችን ቋሚ የስራ ቦታ ባለመስጠቱና፤ አመዳደቡ ሚዛናዊ እንዲሆን ላቀረበለት ጥያቄ፤ ምንም አይነት መልስ ባለመስጠቱ ነዉ። ኬንያዊዉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ጋሽኬ ጊሺሺ፤ ፕሬዝደንት ኬንያታ በአገሪቷ ፍርዳዊነትና ሚዛናዊነት እንደሚኖር ቃል በገቡት ሁኔታ ላይ ጥርጣሪ እንዳለቸዉ ይናገራሉ፤ « በዚህ ረገድ አደርጋለሁ ብለዉ ቃል የገቡት ነገር ተፈጻሚነት ማግኘቱን የሚያሳይ ነገር የለም። የፓርላማ አባላቱ የጋዛ ደምወዛቸዉን በጨመሩበት በአሁኑ ወቅት፤ ሰዎች ተርበዋል። ምንም የተለወጠ ነገር የለም፤ ሁሉ ነገር እንደበር ባለበት ነዉ» ባለፉት ቀናት በርካታ ኬንያዉያን ተቃዉሞአቸዉን ለማሰማት ወደ አደባባይ የወጡት በዚሁ ምክንያት ነበር። በሼዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች፤ የምክር ቤት አባላት የገዛ ደምወዛቸዉን ከፍ ለማድረግ ያቀረቡትን ሃሳብ አልተቀበሉትም። ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በምርጫ ቅስቀሳቸዉ ወቅት እሳቸዉ የሚመሩት መንግስት በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ልጆች ላፕቶፕ «ኮምፒዉተር» እንደሚሰጥ ቃል መግባታቸዉን ተከትሎ ከሳምንት ለበለጠ ግዜያቶች መምህራን አደባባይ ወጥተዉ ተቃዉመዋል። የመምህራኑ ቁጣ ለተማሪዎች ይዉላል የተባለዉ የላፕቶፕ ወጭ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የቀረጥ ወጭን ሲጠይቅ፤ ለመምህራን የደሞዝ ጭማሪ ባለመደረጉ ነዉ። በኬንያ ናይሮቢ የሚገኘዉ የምስራቅ አፍሪቃ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዩንቨርስቲ ሰራተኛ ክላራ ሞማኒ የተቃዉሞ ሰልፉ የተደረገዉ ያለግዜዉ ነዉ ባይ ናቸዉ።« ተቃዉሞ ያሰሙት ሰዎች ፤ በአፋጣኝ ለዉጥን ማየት የሚፈልጉ ናቸዉ። ኬንያታ የመሪነቱን ቦታ ለመዉሰድ ግዜ እንደሚያስፈልጋቸዉ ማሰብ ይገባቸዋል። በምርጫ ግዜ የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ዕድል ልንሰጣቸዉ ይገባል እንጂ ገና ስልጣን በያዙ በ 100ኛ ቀናቸዉ አንድ ፍርድ ላይ መድረስ የለብንም።»የናይሮቢዉ መንግስት አዲስ ካቢኔን ባዋቀረበት በአሁኑ ወቅት፤ ፕሬዝደነት ኬንያታ ከፖለቲካዉ መድረክ ሳይሆን ከሳይንስ ምርምር እንዲሁም ከኤኮነሚ ምሁራን ዘርፍ የመሰረቱት ካቢኔ አግራሞትን ይዞ ብቅ ብለዋል ። የፕሪዝደንት ኬንያታ ይህ አዲስ ስልት ኬንያዉያን ሳያስቆጣ አልቀረም፤ ኬንያዊዉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ጋሽኬ ጊሺሺ እንደሚሉት፤ «ወደ ካቢኔዉ ይዘዋቸዉ የገቡት ሰዎች፤ ለዉጥን በማምጣታቸዉ የታወቁ አይደሉም። እንደዉም አብዛኞቹ የኬንያን ኤኮነሚ ያንኮታኮቱ ናቸዉ»

ጋሽኬ ፕሪዝደንት ኬንያታ የሾምዋቸዉን አዲሱን የኤሌትሪክ ሃይል ሚንስትር ዴቪድ ቸርችርን እንደምሳሌ ይጠቅሳሉ። ዴቪድ ቸርችርን በ 1990 ወደ አንድ ሽህ በላይ ሰራተኞች ጡረታ በተጭበረበረበት የቴሌኮምንኬሽን እና የፖስታ አገልግሎት የመንግስት መስሪያ ቤት አስተባባሪ ሆነዉ አገልግለዋል። የነዚህ መስሪያ ቤቶች አስተባባሪ የአሁኑ የኤሌትሪክ ሃይል ሚንስትር ጥፋተኝነታቸዉን ማረጋገጥ ግን አልተቻለም። የኬንያዉ ፕሪዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ምክትላቸዉ ዊሊያም ሩቶ በስብዕና ላይ በተፈፀመ ግፍ በዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት ይፈለጋሉ። የጦር ወንጀሎችን የሚከታተለውና ኔዘርላንድስ ዴንሐግ የሚገኘው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ICC አቃቤ ሕግ ሁለቱን መሪዎች የከሰሰዉ በኬንያ እጎአ በ2007 እና በ2008 ዓ,ም ከምርጫ በኋላ በተከሰተው ብጥብጥና ግድያ ተጠያቂ ናቸዉ የሚል ነበር። የፍርዱ ሂደት ለመጭዉ መጸዉ የተላለፈ ሲሆን ፕሪዝደንት ኬንያታ ፍርዱ በምስራቅ አፍሪቃ እንዲደረግ ጠይቀዋል። እንደ ፕሪዝደንቱ፤ ጉዳዩ ዴንሃግ ኔዘርላንድ መደረጉ ከመንግስት ጉዳይ ጋር ግንኙነት የለዉም ባይ ናቸዉ፤ ይህን የኬንያታን ሃሳብም የአፍሪቃ ህብረት ደግፎታል። ፕሪዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ስልጣንን ሲይዙ በኔዘርላንድስ ዴንሐግ ከሚገኘው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ጋር ሙሉ ትብብር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዉ ነበር።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic