አፍቃሬ ናዚዎች እና የጀርመን መንሥግሥት ይቅርታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አፍቃሬ ናዚዎች እና የጀርመን መንሥግሥት ይቅርታ

የጀርመን መንግሥት የሠብአዊ መብት ጉዳይ ሐላፊ ማርኩስ ሉኒንግ ጄኔቭ-ለተሰየመዉ ለተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት ሥብሰባ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹ ፈጥነዉ አለመያዛቸዉ ግልፅ ሠብአዊ መብት ረገጣ ነዉ።ሉኒንግ ለተፈጠረዉ ጥፋት በጀርመን መንግሥት ሥም በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።

የጀርመን ፀጥታ አስከባሪዎች አስር ሰዎችን የገደሉ አፍቃሬ ናዚዎችን በፍጥነት ተከታትለዉ ለፍርድ ባለማቅረባቸዉ የሐገሪቱ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ መብት ምክር ቤትን በይፋ ይቅርታ ጠየቀ።የጀርመን መንግሥት የሠብአዊ መብት ጉዳይ ሐላፊ ማርኩስ ሉኒንግ ጄኔቭ-ለተሰየመዉ ለተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት ሥብሰባ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹ ፈጥነዉ አለመያዛቸዉ ግልፅ ሠብአዊ መብት ጥሰት ነዉ።ሉኒንግ ለተፈጠረዉ ጥፋት በጀርመን መንግሥት ሥም በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።ስምንት የቱርክ፥ አንድ የግሪክ ዜጎችን እና አንዲት የጀርመን ፖሊስን ገድለዋል ተብለዉ ከሚጠረጠሩት በሕይወት የምትገኘዉ ተጠርጣሪ የፍርድ ሒደት አሁንም እንዳወዛገበ ነዉ። ስለ ይቅርታዉን ይዘትና መልዕክት ከበርሊኑ ወኪላችንን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ጋር ቃለ ምልልስ አድርገናል ።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic