አፍሪካና የፆታ ሁኔታ | የጋዜጦች አምድ | DW | 04.01.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

አፍሪካና የፆታ ሁኔታ

በስታትስቲክስ ከሰፈረዉ በላይ በርካታ ሴቶች በተለይ በአፍሪካ በድህነት ይገኛሉ። የልማት ፖሊሲ ተግባራዊ ሚና ከሚጫወትበት መንገድ አንዱም በፃታ ላይ የተመሰረተዉ የመረጃ ዉጤትና እሱ ላይ ተመስርቶ የሚወጣዉ እቅድ ነዉ። ድህነትን ለመዋጋት ያለመ ሁሉ የሴቶችን ሚና አገናዝቦ መንቀሳቀስ እንደሚገባዉ እዉነት መሆኑ አያከራክርም።

የተባበሩት መንግስታት የምዕተ ዓመት የልማት ዕቅድም ትርጉም እንዲኖረዉ ይህን መሰሉ ስታትስቲክስ ወሳኝ ነዉ። ይህ ሳይደረግ ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2015ዓ.ም አንዳንድ የልማት እቅዶች ተግባራዊ ለመሆን ቢችሉ እንኳን በርካታ ድሆች ባሉበት ፋይዳዉ ምን ላይ ነዉ? በማለት የዶቼ ቬለዋ ሞኒካ ሆገን ትጠይቃለች። በተጨማሪም ለትምህርት ስርጭቱም ሆነ የኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት ግንዛቤን ለማዳበር እንዲህ ያለዉ መረጃ ያስፈልጋል። ሆኖም ግን እስከ ዛሬ ድረስ የመረጃና የፆታ ስርጭት ብዙም ትኩረት አልተሰጠዉም። አሁን ባለሙያዎች ስለሴቶችና በህብረተሰቡ ዉስጥ ስላሉበት ሁኔታ የሚገልፅ መረጃ መጠየቅ
ጀምረዋል። በዑጋንዳ በተካሄደዉ ዓለም ዓቀፍ የስታትስቲክስ ጉባኤ በአቀራረብ ላይ
ትችት መሰንዘሩን የሚያሳየዉ የሆገን ዘገባ የሚከተለዉ ነዉ።
“የአንድ አገር ዓመታዊ ምርት ጋር በተገናኘ ሁኔታ አይደለም የፆታን ስርጭት መለካት የሚቻለዉ። ወንዶችና ሴቶች ለአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ረገድ ያደረጉትን አስተዋፅዖ ለመመልከት የምንፈልግ ከሆነ ግን የግድ ሌላ ማሳያ የምን ወስድበት አዲስ ስልት መቀየስ ይኖርብናል።
የሚሉት የአፍሪካ የልማት ባንክ በዑጋንዳ በቅርቡ የተካሄደዉ ዓለም ዓቀፍ የስታስትስቲክስ ጉባኤ ተጠሪ ሚሼል ሙዬሎ ካቶላ ናቸዉ።”
በማደግ ባሉት ሀገራት ድህነትን ለመዋጋት የሚደረገዉ ጥረት ትርጉም ያለዉ እንዲሆን እስከዛሬ ከተደረገዉ አካሄድ በተለየ የስታትስቲክስ መረጃዎች ሁሉ በፆታ ተከፋፍለዉ መታየት ይኖርባቸዋል።
ዉብ አባባል ነዉ ሆኖም ወደተግባር መለወጡ ብዙ እንደሚጠይቅ ግልፅ ነዉ። የቦትስዋና ብሄራዊ የስታትስቲክስ ቢሮ ዳይሬክተር አና ማጄላንትሌ የሚሉት አለ
“አዳምጬዋለሁ እናም እስከምን ድረስ እንድንሄድ ይፈልጋሉ አልኩ ይሄ እንደየዘርፉ ይለያያል። ያላሰላነዉ ዘርፍ የቱነዉ? ለምሳሌ ትምህርት ቤት የገቡትን ተማሪዎች ወንድና ሴት በማለት ከፍለን ወይም የህዝቡ ቁጥር ባጠቃላይ ከፆታ አንፃር ወይም ስራ ያለዉ የሌለዉ እያልን እንክፈል? ግን እሱ እንደተናገረዉ በበዓመታዊ የገቢ መጠን ብንል ያ ጥቅል የምጣኔ ሃብትን ብቻ የሚያሳይ ነዉ በፆታ ደረጃ የልተፈረጀም። ለእኛ ለጊዜዉ ግድ የለም። ምክንያቱም የወንዶች አስተዋፅዓ ነዉ የሴቶች ከፍተኛዉ ከማለት በፊት በአገር ደረጃ ያለ እድገትን ነዉ ለማየት የሞከርነዉ። እድገትን ነዉ ለማየት የፈለግነዉ።»
ሆኖም ይህ በቂ አይደለም በምጣኔ ሃብቱ ረገድ የሴቶችን አስተዋፅዖ ለማየት ባለሙያዎች ከየልማት ትብብሮች በርካታና ትክክለኛ መረጃ ይፈልጋሉ።
ባለፈዉ የፈረንጆቹ 2005ዓ.ም የወጣዉ የሲቪል ድርጅቶች ዓለም ዓቀፍ የሶሻል ዎች በየድሃ አገራቱ የሚደረገዉ ድህነትን የማስወገድ ጥረትና የፆታ እኩልነት ላይ ያተኮረ ዘገባ ፆታና ስታትስቲክስን በተመለከተ ያለዉን ስጋት አሳይቷል።
በተለይ ዘገባዉ በየሀገራቱ የተደረገዉን በየቤተሰቡ የሚታየዉን የድህነት መጠን ወይም ገቢን ለማሳየት የተወሰደዉን የመለኪያ መንገድ በእጅጉ ተችቷል።
ሆኖም በቤተሰብ ደረጃ የሚገኘዉ የገቢ መጠን ወይም ማንኛዉም የቤተሰቡ ንብረት ለሁሉም የቤተሰብ አባላት በቀጥታ እኩል ይከፋፈላል ብሎ ገምት ሰንዝሯል። የበርካታ አዳጊ ሀገራት ነባራዊ እዉነታ ሲታይ ግን ይህ እዉነት እንዳልሆነም ዘገባዉ ይጠቁማል።
በየቤተሰቡ የሚገኙ በርካታ ሴቶች ገንዘብ የማግነት እድልም ሆነ ንብረት የማፍራት እድሉን ተነፍገዋል። ይህ ሃቅ ሲታይ ደግሞ በድህነት የሚኖሩት ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ሴቶች ሁኔታ ችላ መባል የለበትም።
በቦትስዋና ይህን ሊያመላክት የሚችል አመቺ ሁኔታም ሆነ ስልት የለም በማለት የስታትስቲክስ ዳይሬክተሯ ማጂላንቴል ያስረዳሉ።
“በተናጠል የመስራቱ ነገር እስከምንድረስ እንደሚያስኬድ ማየት ያስፈልጋል። እእሳሌ የገቢና ወጪ ቅኝት ባደረግንበት ላይ በትምህር፤ በአንዳንድ ንግዶች፣ በፓርላማ፤ በአገሪቱ የተለያዩ ከፍተኛ ደረጃዎች የሴቶችን አስተዋፅዖ አይተናል። ለምሳሌ በፓርላማ ስንት ሴቶች ይገኛሉ? እዚህ ላይ ነዉ የነበርነዉ። ሆኖም በመቀጠል ዓመታዊ ገቢን አስመልክቶ ነጣጥለን ለመስራት ብናስብ ቦትስዋና ዉስት ይሄ የለንም። እንዴት ሊሆን እንደሚችልም አላዉቅም። ምክንያቱም ሁሉንም ዘርፍ መዉስድ የወንዶችና የሴቶች አስተዋፅዖ ብለን መክፈል ይኖርብናል። ለምሳሌ በእርሻዉ ረገድ የወንዶችና የሴቶች አስተዋፅዖ ብዬ ልነግርሽ አልችልም። የለኝም።”
የሴቶችን በምጣኔ ሃብቱም ሆነ ማህበራዊ ሁኔታቸዉን ለማየት ይህን ዓይነቱን የስታትስቲክስ ስልት ለማሳሻል ከ11ዓመታት በፊት ፔኪንግ በተካሄደዉ የዓለም ሴቶች ጉባኤ ሃሳብ ተሰንዝሮ ነበር።
ያም ማለት ለምሳሌ ክፍያ የሌለዉን ስራቸዉን በተመለከተ መረጃ ሲሰበሰብ ስልቱ እንዲሻሻል መደረግ ነበረበት።
ምክንያቱም ከምጣኔ ሃብቱ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም ያለዉ ሆኖም በቤተሰባቸዉ ውስጥ ካሳ የማያገኙባቸዉን በርካታ ተግባራት ማከናወናቸዉ የታወቀ ነዉና።
በካናዳ፤ ኩባ፤ ፈረንሳይ፤ ጣሊያን፤ ሜክሲኮ፤ ኒዉዚላንድ፤ ስፔይንና ቬኒዙዌላ ከወንዶችና ከሴቶች ይልቅ ከፍተኛ ጊዜዉን ለማይከፈለዉ ስራ የሚያዉለዉ የቱ እንደሆነ ለማየት የተደረገ ጥናት ተደርጎ ነበር።
በዉጤቱ እንደታየዉም ሴቶች የበለጠ ጊዜያቸዉን እንዲህ ባለዉ ስራ ተጠምደዉ ያሳልፋሉ። የሶሻል ዎች ዘገባም እንዳሳየዉ የድህነት መጠንን ለመለካት የሴቶች ማህበራዊ መብትና ግዴታ እንዲሁም ንብረት ለማፍራት ያለባቸዉን ማዕቀቦች ጠልቆ ማገንዘብ ያሻል።
በእርግጥ በተናጠል ከየሀገራቱ የተገኘዉ መረጃ የሚናቅ አይደለም ከዚህ ተነስቶም ዓለም ዓቀፋዊ ወደሆነ ድምዳሜ መሻገር ይቻላል።