አፍሪቃ እና የዕዳው ስረዛ ሀሳብ | የጋዜጦች አምድ | DW | 11.06.2005
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

አፍሪቃ እና የዕዳው ስረዛ ሀሳብ

ብሪታንያና ዩኤስ አሜሪካ ብዙ የአፍሪቃ ሀገሮች የተሸከሙት ግዙፍ የውጭ ዕዳ የሚሰረዝበትን ሀሳብ አቅርበዋል።

ሁለቱ ሀገሮችም ለአህጉሩ ተጨማሪ የሰብዓዊ ርዳታ የሚቀርብበት አንድ ፕሮዤ ለማውጣት በጋራ በመሥራት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በአፍሪቃ፡ በተለይም ከሰሀራ በስተደቡብ ባሉት አፍሪቃውያት ሀገሮች የተስፋፋውን የድህነት ሁኔታን ለመቀነስ በምላሹ አፍሪቃውያቱ ሀገሮች የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።