አፍሪቃ እና የኤኮኖሚ ዕድገትዋ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 24.04.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አፍሪቃ እና የኤኮኖሚ ዕድገትዋ

ትናንት በጀርመን ሐምቡርግ የተከፈተው ስድስተኛው የጀርመን-አፍሪቃ የኃይል አቅርቦት መድረክ ይህንን ፈተና እንዴት መወጣት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት ተጀምሮዋል። የአፍሪቃ የኃይል ገበያ ምን ያህል ጠንካራ ነው? ከአፍሪቃስ ጋር በዚሁ ዘርፍ ላይ እንዴት ተባብሮ መስራት ይቻላል?

ዛሬ በጀርመን ሐምቡርግ የተከፈተው  ስድስተኛው የጀርመን-አፍሪቃ የኃይል አቅርቦት መድረክ  ይህንን ፈተና እንዴት መወጣት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት ተጀምሮዋል። የአፍሪቃ የኃይል ገበያ ምን ያህል ጠንካራ ነው? ከአፍሪቃስ ጋር  በዚሁ ዘርፍ ላይ እንዴት ተባብሮ መስራት ይቻላል?

ጋዝ፣ የነዳጅ ዘይት፣ መብራት  በአጠቃላይ የኃይል አቅርቦቱ ጉዳይ የአፍሪቃ እና  የአውሮፓ ትልቅ የወቅቱ  ፈተና ነው።  አንዳንድ ተንታኞች አፍሪቃ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ  ወረት ማንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚያስገኝ ሊዘነጋ እንደማይገባ ይናገራሉ። ግን በአፍሪቃ ያለው የኤኮኖሚ መስክ የተመቻቸ ነውን?

«ታሪካዊ የንግድ እድሎች»፣ «  የአፍሪቃ አገሮች በአለም መድረክ ተሳትፎ» እና ሌሎችም የአፍሪቃ ዕድገት የሚያጎሉ ጽሁፎች በተቋማት አማካሪው ሮላንድ ቤርገር ጥናት ውስጥ ማንበብ ይቻላል። «በወቅቱ አፍሪቃ በኤኮኖሚው ፉክክር ውስጥ የመወዳደር ዐድልዋ ህንድ እና ቻይና ከ 20 አመት  በፊት የነበሩበት ደረጃ ላይ ደርሷል። በአህጉሩ የመካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ቁጥር መጨመር ትልቅ የሸማቾች ገበያ ከፍቷል፣ ይህም ለአለም አቀፍ ገንዘባቸውን ለማሰራት ለሚፈልጉ ሁሉ ብቸኛውን አጋጣሚ ፈጥሮዋል» ይላሉ። ጥናቱን ከፃፉት ውስጥ አንዱ -ክርስትያን ቬዝልስ፤

Arbeiter auf einer Öl-Plattform in Nigeria (undatiert). Der Ölkrieg im Nigerdelta kommt nicht nur Nigeria teuer zu stehen. Kämpfe zwischen verfeindeten Stämmen und der Armee haben internationale Ölgiganten aus dem Delta vertrieben. Der weltweit sechstgrößte Ölproduzent sorgte für weitere Verunsicherung und Preisanstieg auf Ölmarkt, der durch den Irak-Krieg ohnehin angeschlagenen ist. Die Gewaltwelle bedroht auch die für den 19. April angesetzte Präsidentschaftswahl in Nigeria.

የነዳጅ ዘይት ምርት በናይጄሪያ

« በአፍሪቃ ያለው እውነታ ምዕራቡ አለም አንዳንዴ ስለዚሁ አህጉር ከሚያስበው በጣም የተለየ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት እጣ ፋንታቸውን የተቀበሉት አፍሪቃውያን  በበርካታ የሙያ ዘርፍ ስኬታማ እየሆኑ በመምጣታቸው ነው። ጥሬ ሀብት የስኬቱ  አንዱ አካል ብቻ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል። ይህም ሲባል ጥሬ አላባ ወደፊትም ቢሆን  ትልቅ ሚና መያዙ ባይቀርም፣ ትርጓሜውን  በተለይ፣ በመገልገያ እቃ አምራች ኢንዱስትሪ፣ በፊናንሱ መስክ ወይም በመሰረተ ልማቱ ፕሮጀክቶች ካለው ሁኔታ ጋ አዛምዶ ማየት ግድ ይሆናል። » በጥናቱ መሰረት፣  ለታየው ዕድገት የኃይሉ አቅርቦቱ ዘርፍ ድርሻ አበርክቶዋል። ይህ ለአስርተ አመታት መንግስታቱ ችላ ብሎት የቆየው ዘርፍ በሚመጡት 5 አመታት ውስጥ ትልቅ ለውጥ ያስገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ በመህጻሩ ኔፓድ በሚል በሚታወቀው የልማት አጋርነት ለአፍሪቃ ተቋም  የኃይል መርሀ ግብር ኃላፊ  የሆኑት ሞሳድ ኤልሚስሪ ይገምታሉ።

« የአፍሪቃ ህዝብ እየጨመረ ነው። የዛኑ ያህል አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ማግኘት የሚፈልገውም ህዝብ። ኢንዱስትሪውም እያደገ ነው። የአፍሪቃን ጥሬ አላባ የሚፈልጉ ያደጉ አገራት ፍላጎትም እንዲሁ ከፍ ብሏል። ይህ ሁሉ የኃይል አቅርቦቱ መስክ እንዲዳብር ግፊቱን ያጠናክራል። የአፍሪቃ ሕዝቦችም መንግስቶቻቸው ለዚሁ ርዕስ ትኩረት እንዲሰጥ ጫና ያደርጋሉ።»

« አንዳንድ እርምጃ የወሰዱ ብዙ አፍሪቃውያን መንግስታት፣ ለምሳሌ  ግዡፍ የውሀ የኃይል ምንጭ ፕሮጀክት የከፈቱ እንደ ዪጋንዳ እና ኢትዮጵያ ያሉ አገራት አሉ» ይላሉ ኤልሚስሪ።  «ፀሐፊው ይቀጥላሉ፤« እንዲያም ሆኖ በበርካታ የአፍሪቃ አገራት የኃይል አቅርቦቱ በፍጹም በቂ አይደለም። በገጠሩ አካባቢ ከየአስሩ አንዱ ብቻ ነው መብራት የሚያገኘው።  በአገራቱ መዲናዎችም ቢሆን  ቋሚ የመብራት አቅርቦት ስለሌለ የድርጅቶች እድገት በዚህ ምክንያት ተሰናክሎዋል።  »

Tekeze Staudamm, Äthiopien beim Bau 2007, Ferstiggestellt im Februar 2009. www.internationalrivers.org/en/node/3173 +++CC/International Rivers+++ augenommen: 08.2007 hochgeladen: 10.01.2011 Lizenz: http://creativecommons.org/licenses/by-nc-sa/2.0/deed.de

የተከዜ የውሀ ምንጭ ፕሮጀክት

በሀምቡርግ የሚገኘው በምህጻሩ GIGA የተሰኘ ዓለም አቀፍና ያካባቢ ጥናት ተቋም   የአፍሪቃ ምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ሮበርት ካፕል  የሮላንድ ቤርገር አይነት ጥናቶችን በጥንቃቄ ነው የሚመለከቱዋቸው።

« ይህ ባለወረቶችን ገንዘባቸውን በአፍሪቃ እንዲያሰሩ ለመሳብ የሚደረግ ትንበያ ነው፤ ይሁንና እውነታውን መመልከት ይኖርብናል። አፍሪቃ ከአለም ገበያ ቀስ በቀስ እየተገለለች ነው። በኢንዱስትሪው ዘርፍ ጨርሶ ምንም አይነት ሚና የላትም።  በአለም አቀፉ ደረጃ በኤክስፖርት ከሚላከው የኢንዱስትሪ ምርት መካከል የአፍሪቃ ድርሻ 0. 5 ከመቶ ብቻ ነው ። ይህ መጠን ባለፉት 20 አመታት በግማሽ ቀንሷል። እና ሁሉ ነገር ጥሩ እንደሆን አድርጎ ማቅረብ አያስፈለግም። ትክክለኛውን ሁኔታ ለማወቅ ያለውን ችግር በግልጽ መጥቀስ ያስፈልጋል። »

ለካፕል ትልቁ የአፍሪቃ የኢኮኖሚ ችግር ያለው በኢንዱስትሪ እና በግብርናው መስክ በቂ አነቃቂ ኃይል መጓደሉ ላይ  ነው። በርግጥ የዓለም ባንክ ጥናት እንደሚያሳየው ከፍተኛው የአፍሪቃ ኢኮኖሚ ዕድገት መሰረት በጥሬ አላባው ላይ ነው። የአፍሪቃ ኤኮኖሚ በማደግ ላይ መሆኑ አይካድም፤ ግን፣ ሕዝቡ የዕድገቱ ተጠቃሚ አልሆነም። በአንጻሩ በብዙው የአህጉሩ ከፊል ድህነት እየጨመረ ነው።ይሁን እና እድገቱ በማህበረሰቡ ዘንድ አልተዳረሰም። ይልቁንስ በአህጉሯ ሰፊው ክፍል ድህነት ተስፋፍቷል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 24.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14jcA
 • ቀን 24.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14jcA