አፍሪቃ እና አንደኛ የጋዳፊ ሙት ዓመት | አፍሪቃ | DW | 19.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አፍሪቃ እና አንደኛ የጋዳፊ ሙት ዓመት

ኮሎኔል ሙአመር ኧል ጋዳፊ ከተገደሉ እነሆ ዛሬ አንድ አመት ሆናቸው። እኝህ ሰው ላለፉት 41 ዓመታት በአገራቸው ሊቢያ ብቻ ሳይሆን በብዙ የአፍሪቃም መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ፣እንዲሁም፣ በፖለቲካው ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

ራሳቸውን «የአብዮት መሪ ወንድም» ወይም « የነገስታት ንጉስ» እያሉ ይጠሩ የነበሩት ሙአመር ኧል ጋዳፊ ብዙ ገፅታዎች ነበሩቸው። ለምዕራብ አገሮች ጋዳፊ፣ አምባገነን፣ ጨካኝ እና ከማህበራዊ ወግ ያፈነገጡም ነበሩ። ጋዳፊ ከተገደሉ ከአንድ አመት በኋላ አፍሪቃ ውስጥ በምን ይታወሳሉ?የዮጋንዳ የመንግስት ቃል አቀባይ ፍሬድ ኦፖሎት« ጋዳፊ ለብዙ አመታት የዮጋንዳ ወዳጅ ነበሩ። በዮጋንዳ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ንቅናቄ ውስጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጋዳፊ በዮጋንዳ ታሪክ ውስጥ አንድ ቦታ ይኖራቸዋል።»

epa02975684 A Libyan rebel fighter paints on the wall of one of the pipes where Muammar Gaddafi allegedly found hiding, in Sirte, Libya, 21 October 2011. Libyan deposed leader Muammar Gaddafi was arrested on 20 October, some witnesses said he was found hiding in a drainage pipe in Sirte. He died later, along with his son Motassim. EPA/GUILLEM VALLE +++(c) dpa - Bildfunk+++

የጋዳፊ የመጨረሻ መሸሸጊያ

በአጠቃላይ 375 ሚሊዮን ዶላር ጋዳፊ ዮጋንዳ ላይ አፍሰዋል። ከነዳጅ ሽያጭ የተገኘውን የሊቢያ ገንዘብ ፤ በዮጋንዳ ቴሌኮሚኒኬሽን ድርጅት እና ትሮፒካል ባንክ ላይ ውሏል።በዮጋንዳ መዲና ካምፖላ በጋዳፊ ስም የተሰየመ መንገድ እና መስጊድ ይገኛል። ጋዳፊ የአፍሪቃ ምጣኔ ሀብትን የሚያወድሱ ሰው ነበሩ። በመላው አህጉር የሊቢያ መዋለ ንዋይ ይታያል። በኬንያ እና ጋና ቅንጡ ሆቴሎች፣በላይቤሪያ ፤ የጎማ ዛፍ ፋብሪካዎች ፣ በጊኒ የፍራፍሬ ምርት እንዲሁም በምስራቅ አፍሪቃ የቴሌኮሚኒኬሽን እና ነዳጅ ማዲያዎች የሚጠቀሱ ናቸው።

ይሁንና በሊቢያ አብዮት ጊዜ የአፍሪቃ ሀገራት የተመድ የመፍትሄ ሀሳብን በመከተል ጋዳፊ እና ቤተሰባቸው በውጭ ሀገር ያላቸው ሀብት እንዲታገድ ነበር የተስማሙት። እርግጥ ዛሬ ይህ ማዕቀብ ተነስቷል። የሊቢያ የመዋዕለ ንዋይ መስሪያ ቤት LIAም በአገልግሎት ላይ ይገኛል። የመንቀሳቀሻ ገንዘቡ ግን ከሊቢያ አመፅ በፊት የተገኘ ነው። አዲሱ የሊቢያ መንግስት የት እና ምን ያህል ገንዘብ በውጭ ሀገር ዛሬም ተሸሽጎ እንደሚገኝ አያውቅም።

A Libyan man carries bags of food as he walks through a street in Sirte on October 28, 2011. NATO decided to end its mission in Libya on October 31, declaring it fulfilled its 'historic mandate' to protect civilians as contact was made with Moamer Kadhafi's fugitive son. AFP PHOTO/PHILIPPE DESMAZES (Photo credit should read PHILIPPE DESMAZES/AFP/Getty Images)

የሲርተ ከተማ፤ ሊቢያ

ለበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት የጋዳፊ ሞት ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራ ነው ይላሉ የምዕራብ አፍሪቃ ተንታኝ ሰባስቲያን እስፒኦ ጋርብራህ።« በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት በሊቢያ የንግድ ተሳትፎ ደስተኞች አይደሉም። አብዛኞቹም መዋለ ንዋዩን ለአዲሱ የሊቢያ መንግስት አላስረከቡም። ምንም እንኳን በዲሞክራሲያዊ አሰራር አዲሱን መንግስት ቢቀበሉም፤ ድርሻቸውን ገና አላስረከቡም። »

አክለውም ተንታኙ አንዳንድ የአፍሪቃ ሀገራት እንደውም በሊቢያ ካለው አለመረጋጋት አትራፊ እንደሆኑም ገልፀዋል። ከጋዳፊ ግድያ አንድ አመት በኃላ አዳዲስ ሰዎች ወደ አፍሪቃ ህብረት መድረክ እየተቀላቀሉ ነው። በእንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ኃላፊነት ደቡብ አፍሪቃ በአፍሪቃ ህብረት የበለጠ ድምፅ ሊኖራት ይችላል። በምጣኔ ሀብታዊ ምዋለ ንዋዩም በኩል ቢሆን አዳዲስ እንደ ቻይና ያሉ አገሮች ይገኛሉ። መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው እና 200 ሚሊዮን ዶላር ያወጣው የአፍሪቃ ህብረት የቻይና ሽልማት ነው።

ቬራ ኬርን

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic