አፍሪቃ እና ሶፍትዌር | ባህል | DW | 04.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

አፍሪቃ እና ሶፍትዌር

በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በኢንተርኔት አማካይነት በቀላሉ የሚገኙ መረጃ እና አገልግሎቶችን ተጠቅሞ እውቀትን እንዴት ማዳበር ይቻላል የሚሉ ጥያቄዎች ከሰኞ እስከ እሮብ በቆየው እና ዶይቸ ቬለ ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው።

ኤም- ፔዛ የተንቀሳቃሽ ስልክን ተጠቅሞ ገንዘብ የመክፈያ ወይም የማዘዋወሪያ ዘዴ ነው። አፍሪቃ ውስጥ 2/3 ኛው ኬንያዊ ይጠቀመዋል። ይህም የኮምፒውተር ሶፍት ዌር ከአፍሪቃ አልፎ ሀሳቡ ወደ አፍጋኒስታን እና ሮሜንያ ተላልፏል። ይህ የመክፈያ ዘዴ ግን ዝና ከአተረፈ ሰባት አመታት ተቆጠሩ። አፍሪቃ ውስጥ እነዚህንስ የሶፍትዌር እድገቶች ተጠቅሞ እውቀትን እንዴት ማዳበር ይቻላል። የአፍሪቃ የሶፍት ዌር ባለሙያዎች የነገ ተስፋ ምን ይሆን? ምናልባት በጤና ጥበቃ ላይ ይሆን?

«በአጭር የፁሁፍ መልዕክት በSMS አማካይነት እንዴት ልጄን ልንከባከብ እንደምችል ተምሬያለሁ።ባለቤቴ ነው ስለዚህ የነገረኝ መጀመሪያ እሱ ተመዝግቦ መልዕክቱን ላከልኝ እና ኃላ ላይ እኔ ራሴ ተመዘገብኩ።»ትላለች እመጫቷ ታንዛኒያዊ ሜሊሳ አሊ።« ሄልዚ ቤቢ» -ጤናማ ልጅ የሚለው የስልክ የጤና አገልግሎት ከሚደርሳቸው 400 ሺ ሰዎች አንዷ ናት። በአፍሪካ የጤና ዘመቻን አስመልክቶ የሚገኝ ትልቁ በስልክ የሚቀርብ አገልግሎት ነው። ለእናቶች እና ለልጆች ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን እናትየዋ ገና እርጉዝ ሳለች ነው በስልክዋ መገልገል የቻለችው። ቴክኒኩን ያበለፀጉት ኔዘርላንድስያዊ ባስ ሆፍማን ይባላሉ።

« በታንዛንያ የጤና ሚኒስቴር ኃላፊነትና በአጋርነት የሚሰራ ነው። የዚህ ስኬት ተካፋይ የሆኑ በርካታ ድርጅቶች አሉ። በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም የቴሌኮሚኒኬሽን አቅራቢዎች አብረው ይሰራሉ። እንደሚመስለኝ አጋርነት ባይኖር ኖሮ እንደዚህ አይነት እውቀት ላይ ራሱ ይደረሳል ብዬ አላስብም።»

እዮብ በሻህ ኢትዮጵያዊ የሶፍት ዌር ባለሙያ ነው። እንደ « ሄልዝ ቤቢ» አይነት ባይሆንም እዮብም ለጤና የሚጠቅም ሶፍት ዌር አዘጋጅቷል።የ29 ዓመቱ ወጣት ከአዋሳ ዮንቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ተመርቋል። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ለሁለተኛ ዲግሪው የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እየተማረ ነው። ከስራው ጎን ለጎን በተጨማሪ በግሉ አዲስ ነገር ለመስራት ይጥራል።እስካሁን በሶስት አይነት የሶፍት ዌር ስራዎች ለመካፈል ችሏል።እዮብ የሚሰራቸው ሶፍት ዌሮች እንደ ፕሮጀክቱ ይለያያሉ። አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች የሙያ ባልደረቦቹ ጋር ነው የሚሰራው። አንዳንዴ ደግሞ ብቻውን ነገር ግን የኢንተርቴቱ ችግር እንደ እዮብ ላሉ የሶስት ዌር ባለሙያዎች በሙያቸው ገፍተው እንዳይሄዱ እና አዳዲስ ነገሮችን እንዳይፈጥሩ መንገዱ የታገደ ይመስላል።

በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በኢንተርኔት አማካይነት በቀላሉ የሚገኙ መረጃ እና አገልግሎቶችን ተጠቅሞ እውቀትን እንዴት ማዳበር ይቻላል? የሶፍት ሄር ባለሙያዎችስ ምን ችግር ይገጥማቸዋል። ሙሉ ዝግጅቱን ከድምፅ ዘገባው መስማት ይቻላል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኃላ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች