«አፍሪቃ በነብር እና በደራጎን መካከል» | ዓለም | DW | 30.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

«አፍሪቃ በነብር እና በደራጎን መካከል»

ለአራት ቀናት ኒዉዴሊህ ላይ የተካሄደዉ የሕንድ እና አፍሪቃ ምጣኔ ሐብታዊ ጉባኤ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ለየት የሚያደርገዉ በርካታ የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች መሳተፋቸዉ ነዉ። ሕንድ ብቻ ሳትሆን ቻይናም ከአፍሪቃ ጋር የምጣኔ ሐብት ጉባኤዎች ታደርጋለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:21
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:21 ደቂቃ

አፍሪቃ በነብር እና በደራጎን መካከል

ሕንድ ከአፍሪቃ ጋር የምታደርገዉን የንግድ ልዉዉጥ የቻይናዉ በብዙ እጅ ይበልጠዋል። የሁለቱ የእስያ ባለግዙፍ ኤኮኖሚ ሃገራት በሚያደርጉት ዉድድር አፍሪቃ በነብር እና ደራጎን መካከል ያለች አስመስሏታል።

ከጉባኤዉ መጨረሻ ሕንዶች መልካም ነገር ማግኘታቸዉ እሙን ነዉ። ከአፍሪቃ ዉጪ በተካሄደ ጉባኤ በርካታ የአፍሪቃ መሪዎች ሲካፈሉ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ። ጉባኤዉ ለሕንድ ለምን አስፈለገ? በኅዳር ወር ማለቂያ ላይ ደቡብ አፍሪቃ የቻይና አፍሪቃ ጉባኤን ታስተናግዳለች። «በአዲሱ አፍሪቃን የመቃራመት» መርሕ ማለትም አዲስ ተዘዋዋሪ ቅኝ የመግዛት ፉክክር ሕንድ፤ ጎረቤቷ በጥሬ ሀብት ስትበለጽግ ማዘኗ አይቀርም። ለነገሩ ቻይና ከአፍሪቃ ጋር የምታካሂደዉ የንግድ ልዉዉጥ የሕንዱን በሶስት እጅ እጥፍ ይበልጣል። የሕንድና አፍሪቃ የንግድ ልዉዉጥ 70 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ነዉ። ያም ቢሆን ግን መርሃግብሩም ሆነ የጋራ መሠረቱ ሲታይ ከአንበሳዋ አፍሪቃ ጋር ለሚኖራቸዉ ግንኙነት ነብሯ ሕንድ፤ ከደራጎኗ ቻይና ባልተናነሰ ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ማሰቧ የግድ ነዉ።በተመድ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የምትሻዉ ሕንድ የተመድ ሥለአየር ንብረት ፓሪስ ላይ ባዘጋጀዉ ሥብሰባ፤ ዓለም አቀፍ ሽብርን መከላከል፤ እንዲሁም የባህር ላይ ዉንብድናን ለመከላከልና የባህር ላይ የፀጥታ ትብብርን በሚመለከት ለምታቀርበዉ ማሻሻያ ሃሳብ ድጋፍ ትሻለች። አፍሪቃዉያንም በታኅሳስ ወር ናይሮቢ ላይ በሚካሄደዉ የዓለም የንግድ ድርድር ላይ ሕንድን ለስልታዊ ጉድኝት ይፈልጓታል። ለዚህም ኒዉዴሊህ ለልማት እርዳታና ብድር በቢሊዮን የሚገመት ዶላር ለመስጠት ቃል ገብታለች። ሁለት ወገኖች ሲጣሉ ሶስተኛዉ ይደሰታል እንደሚባለዉ፤ የንግድ፤ የፀጥታ ትብብር፤ የአየር ንብረት ለዉጥ እንዲሁም ደቡብ ከደቡብ ትብብርን በሚመለከት የጋራ ስምምነት ከተደረሰ አፍሪቃም ልትጠቀም ትችላለች።

ሕንዳዉያን አስተያየት ሰጪዎች ከጉባኤዉ አስቀድሞ ይህን ታሪካዊ ጉባኤ በሚመለከት ከአፍሪቃ ወገን መጠነኛ ደስታ እና ደካማ ዝግጅት መኖሩን በመጠቆም አግራሞታቸዉን ገልጸዋል። ይህንን ለረዥም ጊዜ ላስተዋለ ብዙ ላያስገርም ይችላል። በኤኮኖሚ የገፋችዉ ደቡብ አፍሪቃ ለረዥም ዘመናት ለሕንድ ከሰል አቅራቢ ናት። ሆኖም ግን 1,3 ሚሊየን የሕንድ ዝርያ ያላቸዉ ዜጎች ለሚኖሩባት የማንዴላ ሀገር የንግድም ሆነ የእዉቀት ሽግግር አልተደረገም። ይህ ደግሞ በታላቅ ተስፋ በተመሰረተዉ ብሪክስ በመባል በሚጠራዉ እና ብራዚል፤ ሩሲያ፤ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃን ባሰባሰበዉ ትብብርም የሚታይ ነዉ። የብራዚል ልዑካን ለደቡብ ደቡብ ትብብሩ ሕይወት ለመስጠት እስካሁን ከደቡብ አፍሪቃ አንድ ወኪል እንኳ የሚያገኙበት አድራሻ እንደሌላቸዉ በይፋ የሚወቅሱት ጉዳይ ነዉ። አፍሪቃ ዛሬም በግንባር ቀደምትነት ጥሬ ዕቃ ላኪ ናት። እንቁዋ፣ የተዘጋጁ ጌጣጌጦቿ፤ የነዳጅ ዘይቷ በተጠቃሚዎች ዘንድ ጥራቱ ዝቅ ተደርጎ ይታያል፤ ለዚህ ግን ዴሊህ እና ቤጂንግ ሳይሆኑ ናይጀሪ እና ደቡብ አፍሪቃ ናቸዉ ተወቃሾች።

ሕንዳዉያን አስተያየት ሰጪዎች በአሁኑ ጊዜ የፀጥታ መርህን አስመልክቶ የጋራ እና ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራት አፍሪቃን ማበረታታቸዉ አስደሳች ነዉ። ለምሳሌ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሕንድ፤ ካለ አፍሪቃ ህብረት ድጋፍ የሕንድ የሰላም አስከባሪዎችን አፍሪቃ ዉስጥ ለማሰልጠን እንዴት ይወስናሉ? ሌላዉ ጥያቄ እንዴት አፍሪቃ ከሌሎች ጉዳዮች በላይ በጤናዉ ዘርፍ ከሕንድ ጋር በጋራ ለመሥራት በይፋ ተስማማች የሚለዉ ነዉ። እንደሻዶምስኪ ገለፃ፤ በግዙፉ የሕንድ አፍሪቃ ጉባኤ፤ አፍሪቃ እንደተጓዳኝ ሳይሆን እንደተጋባዥ ነዉ የተገኘችዉ። የቻይናን የኤኮኖሚ መስፋፋት የተመለከቱት የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር «ኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ ያለዉ በረዶ እንዳይቀልጥ» አፍሪቃ ላይ መዋዕለ ንዋያችንን ማፍሰስ አለብን በሚል ነዉ የተነሱት። ከአራት ቀናቱ ጉባኤ በኋላ አንድ ሺህ የሚሆኑት ልዑካን ከቻይናዉ ደራጎን ይልቅ የሕንዱ ነብር አቀራረብ ሳይስባቸዉ አይቀርም። በዚህ ጉባኤ ላይ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት የእስራት ማዘዣ የተቆረጠባቸዉ፤ የሱዳኑ ኦማር አልበሽርም ተጋብዘዋል። አፍሪቃን እንደበማደግ ላይ ያለ ገበያ የመረጠዉ የሕንድ መንግሥታዊ የነዳጅ ኩባንያ ሱዳን ዉስጥ መሬት አለዉ። አፍሪቃ በድራጎን እና በነብር መካከል የሚካሄደዉን ሩጫ ትታዘባለች። አንበሳዉም ይህን ያስተዉላል።

ሉድገር ሻዶምስኪ/ ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic