አፍሪቃውያን ስደተኞች በእስራኤል | አፍሪቃ | DW | 21.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አፍሪቃውያን ስደተኞች በእስራኤል

የአፍሪቃውያን ስደተኞች ጉዳይ ተመልካች ድርጅት ስራ አስኪያጅ፤ አቶ ዮሀንስ ባዩ እንዳሉት እስራኤል ውስጥ በአፍሪቃውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው የጥላቻ ጥቃት ተጠናክሯል።

ወደ እስራኤል የሚጎርፉት አፍሪቃውያን ቁጥር በብዛት መቀጠሉን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትናያሁ ትናንት አስታወቁ። «ይህንን መጉረፍ ካላቆምን ቁጥሩ ባንዴ ከ60 ሺ ወደ 600 ሺ ከፍ ይላል» ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ወደ እስራኤል በርካታ አፍሪቃውያን እየተሰደዱ እንደሆነ ይነገራል በብዛትም በግብፅ በኩል አድርገው በርካታ ኤርትራዊያን እና ሱዳናዊያን ይሰደዳሉ። ባለፉት ሳምንታት አንድ እስራኤላዊ ደቡባዊ ቴላቪቭ አፍሪቃውያን ስደተኞች በሚኖሩበት ህንፃ ላይ ጠርሙስ ውስጥ የተሞላ ቤንዚን በእሳት አያይዞ ጥቃት ማድረሱ የሚታወስ ነው። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አፍሪቃውያን ስደተኞች ላይ በብዛት በደቡናዊ ቴላቪቭ የሚደርሰው ጥቃት በአፍሪቃውያን ላይ ጥላቻ ስላለ ነው ይላሉ  የአፍሪቃውያን ስደተኞች ጉዳይ ተመልካችን ድርጅት  ስራ አስኪያጅ፤ አቶ  ዮሐንስ ባዩ። አቶ ዮሐንስ የአፍሪቃውያን ስደተኞች ጉዳይን የሚመለከት በእንግሊዘኛው ምህፃር ኤ አር ዲሲ በመባል የሚታወቅ የአፍሪቃውያን ስደተኞች ጉዳይ ተመልካችን ድርጅት ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ናቸው። አፍሪቃውያን ስደተኞች ላይ ስለሚደርሰው ጥቃት እና ጊዜያዊ ሁኔታ ከአቶ ዮሐንስ  ጋ የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምምልስ ያድምጡ።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 21.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14zQa
 • ቀን 21.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14zQa