አፍሪቃዉያን ያልተገኙበት የአፍሪቃ ጉባኤ በአሜሪካ  | አፍሪቃ | DW | 22.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

አፍሪቃዉያን ያልተገኙበት የአፍሪቃ ጉባኤ በአሜሪካ 

በዩናይትድ ስቴትስ የተደረገው አራተኛዉ የአፍሪቃዉያን ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሃብትና ልማት ጉባኤ አፍሪቃዉያንን ባላሳተፈ መልኩ መካሄዱ ተገለጸ። ጉባኤዉ ላይ መገኘት ከነበረባቸዉ እና የይለፍ ፈቃድ ማለትም ቪዛ ከተከለከሉት ሃገራት ኢትዮጵያ፣ ጊኒ፣ ሴራሊዮን፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪቃ እና ናይጀሪያ ይጠቀሳሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:38

የአፍሪቃ ጉባኤና የቪዛ ክልከላ

የተፈጠረዉ አጋጣሚም የጉባኤዉን አስተናጋጆች ጭምር አስገርሟል።በአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ይህን አስመልክተዉ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ምላሽ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ገልጸዉ፤ የኤምባሲዉ ሠራተኞች ሕግን ተከትለዉ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።  ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic