አፍሪቃዉያን በአፍሪቃ ያለቪዛ | አፍሪቃ | DW | 18.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

አፍሪቃዉያን በአፍሪቃ ያለቪዛ

የአፍሪቃ ኅብረት ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2018 ዓ,ም ጀምሮ አፍሪቃዉያን በአህጉሪቱ ያለምንም ይለፍ ፈቃድ ወይም ቪዛ ከአንዱ ሃገር ወደሌላዉ መዘዋወር እንዲችሉ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ ካደረገ ቆየ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:32

አፍሪቃዉያን ያለቪዛ

ትናንት ኪጋሊ ሩዋንዳ ላይ በተጀመረዉ የአፍሪቃ ኅብረት ጉባዔ ላይም ይኸን ለረዥም ጊዜ የተጠበቀ የፓን አፍሪቃ የይለፍ ሰነድ ይፋ አድርጓል። በተቃራኒዉ የተባለዉ ያለ ይለፍ ፈቃድ በአፍሪቃ ሃገራት መንቀሳቀስ ተግባራዊ የማይሆን ለስም ብቻ የሚደረግ ነዉ የሚሉ አሉ፤ ስደትን ያባብሳል የሚሉም ጥቂቶች አይደሉም። ይህን በሚመለከት የኢትዮጵያዉያን አስተያየት ምን ይሆን? አንዳንዶችን ጠይቀናል።


ዮሐንስ ገብረግዚአብሄር


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic