አፍሪቃዉያን ስደተኞች በፓሪስ | አፍሪቃ | DW | 11.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አፍሪቃዉያን ስደተኞች በፓሪስ

በማዕከላዊ ፓሪስ የሚገኘዉ ላሻፔል የተባለዉ ሥፍራ ለወትሮዉም ቢሆን ድንበር አቋርጠዉ ወደፈረንሳይ ለገቡና ወደፓሪስ እግር ለጣላቸዉ ተሰዳጆች እንደመነኻሪያ የምትቆጠር ናት ትላለች የፓርሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ።

ሆኖም ግን የሰሞኑ አክራሟ ከወትሮዉ የተለየ መልክ አሰጥቷታል። እንደሃይማኖት ዘገባም ከተማዉን አቋርጦ ከሚሄድ የከተማ ባቡር ድልድይ ሥር የተተለኩት ሰማያዊና አረንጓዴ ትናንሽ ድንኳኖች ለአካባቢዉም ሆነ ለከተማዉ አዲስ ክስተት ሆኗል።

Flüchtlinge im Paris la Chapelle

የስደተኞቹ መጠለያ ድንኳኖች በፓሪስ ጎዳና

በዚህ ስፍራም ቁጥራቸዉ ወደሁለት መቶ የሚጠጉ አብዛኞቹም ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራና ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች ናቸዉ። ከተሰዳጆቹ ዉስጥም ነፍሰጡሮችና በርካታ ሴቶችም ይገኙበታል። ስደተኞቹን ከፈረንሳይ መንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ እስካሁን ባለማግኘታቸዉም እዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በጎ አድራጊዎች ሰብዓዊ እርዳታ እያደረጉላቸዉ ነዉ። ተሰዳጆቹን በስፍራዉ ሄዳ ያነጋገረቻቸዉ ሐይማኖት ከፓሪስ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።

ሐይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic