አፍሪቃዉያን ስደተኞች በማልታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አፍሪቃዉያን ስደተኞች በማልታ

ከሊቢያ ወደጣሊያንና ማልታ የሚፈልሱ አብዛኛዎቹ የኤርትራ ዜጎች የሆኑ የአፍሪቃ ስደተኞች እንቅስቃሴ መቀጠሉን የሮሙ ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረእየሱስ የላከዉ ዘገባ ያመለክታል። በቅርቡ የሜዲትራኒያን ባህርን በጀልባ አቋርጠዉ ወደጣሊያን ያመሩ፤

Burashada Camp in Gharyan, Libyen (Juni 2012; Credit Sara Prestiani). Die Migranten werden den ganzen Tag lang in Zellen eingeschlossen. Copyright: Sara Prestiani

Migranten in Libyen

 250 ስደተኞች ለችግር ተጋልጠዉ በማልታ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ህይወታቸዉ ተርፏል። ስደተኞቹ ሊቢያ ቤንጋዚ ላይ ለመኖር የሚያስችላቸዉ ህጋዊ ፈቃድ ስለሌላቸዉ ከታሰሩበት ወህኒ ለመዉጣትና ወደአዉሮጳ ሀገሮች ለመጓዝ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማንነታቸዉ ባልታወቀ የሊቢያ ዜጎች የተጠየቁ ሲሆን ከፍለዉ የወጡትም ቢሆኑ ቤንጋዚ ላይ በአንዲት ስፍራ ታግተዉ ለመቆየት ተገደዋል። በዚሁ ስፍራም የአንድ ስደተኛ ህይወት አልፏል። በማልታ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ርዳታ የተረፉት ወገኖች ለተመ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ባለስልጣናት እንደገለፁት ለሁለት ቀን የሚሆን ዉሃ ምግብ የሰጧቸዉ ህገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎች በአነስተኛ ጀልባ ጭነዉ ባህር ላይ ነዉ የለቀቋቸዉ።

ተኽለእግዚ ገብረኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic