« አፋርዬ ሃዬ» እና ካሌብ አርአያ-ሥላሌ | ባህል | DW | 13.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

« አፋርዬ ሃዬ» እና ካሌብ አርአያ-ሥላሌ

ተዋናይ ፣ ሞዴል እና በቅርቡ ደግሞ የሙዚቃውን ዓለም የተቀላቀለው ድምፃዊ ካሌብ አርአያ-ሥላሌ የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችንን ነው።

ብዙዎች በተከታታይ በሰው ለሰው ድራማ ላይ ልዑልን ሆኖ ሲጫወት ያውቁታል። በቅርቡ ደግሞ ይህ ወጣት ተዋናይ አዲስ የሙዚቃ ቪድዮ ይዞ ብቅ ብሏል። ድምፃዊ ካሌብ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ስለ ሙዚቃ ስራ ሲመካከር የአፋር ክልል እንደ ሌሎች ክልሎች ብዙ የሙዚቃ ቪዲዮ ያልተሰራበት ሆኖ በማግኘታቸው ወደ አፋር ሄዶ ለመቅረፅ እና ቦታውን ለማስተዋወቅ እንደወሰነ ይናገራል።

የሙዚቃውን ቪዲዮ እንዲሰራ ቀኝ እጁን የሰጠው ደግሞ ከአራት ዓመት በፊት የፊልም ስራን በግሉ የጀመረው የፊልም ዳሬክተር ፍሬዘር አትክልት ነው። ስለ « አፋርዬ ሃዬ» የቀረፃ ስራ ሲናገር፤ እስካሁን ከሰራቸው ቀረፃዎች ከባዱ ነበር ይላል።ካሌብ እና ፍሬዘር ይህንኑ ቪዲዮ ለመቅረፅ አንድ ሳምንት ፈጅቶባቸዋል። በአይነቱ ለየት ይበል እንጂ ፍሬዘር ቪዲዮ ሲቀርጽ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። የሌሎች የበርካታ አርቲስቶች የሙዚቃ ቪዲዮዎችም ቀርፆ አቀናብሯል። ለመሆኑ ይህ አጋጣሚ ለፍሬዘር ምናልናትም ለሌሎች የፊልም ባለሙያዎች ምን ያህል የስራ ዕድል ከፍቷል ? ፍሬዘር አስተያየቱን ሰጥቶናል።

አርቲስት ካሌብ አርአያ-ሥላሌ እና የፊልም ዳሬክተር ፍሬዘር አትክልት በወጣቶች ዓለም ዝግጅት የነበራቸውን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic