አፅናፋዊ የምጣኔ ሕብት ትስስር | በማ ድመጥ መማር | DW | 15.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

አፅናፋዊ የምጣኔ ሕብት ትስስር

ዝግጅታችን አፅናፋዊ የምጣኔ ሃብት ትስስር በአፍሪቃ የሚ ያሳድረውን ተፅዕኖ በጥልቀት ይመረምራል፦ ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት ትስስርን ያመጡና በዚህ ምክንያትም የተጎዱትን ወገኖች ያቀርባል::

የአፍሪቃ ጠላትና ወዳጅ

በማዳመጥ መማር አፅናፋዊ የምጣኔ ሃብት ትስስር (ግሎባላይዜሽን) በአፍሪቃ የሚ ያሳድረውን ተፅዕኖ በጥልቀት ይመረምራል። ዝግጅታችን ዓለም አቀ የምጣኔ ሃብት ትስስርን ያመጡና በዚህ ምክንያትም የተጎዱትን ለአድማጮቹ ያቀርብላቸዋል:: ይህ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ሰዎችን እንዴት ከድህነት መንጭቆ እንዳወጣቸውና አንዳንዶቹን ደግሞ እንዴት በድህነት አረንቋ ውስጥ እንደከተታቸው ያሳያል::

በዓለም አቀፍ አፅናፋዊ የምጣኔ ሃብት ትስስር ዙርያ ሂስ የሚ ሰጡ አካላት ናይሮቢ ውስጥ በተሰበሰቡበት ወቅት ለዓለም አቀፍ የማ ኅበረሰብ መድረክ 2007 ያቀረቡት መልእክት ግልፅ ነበር። አፍሪቃውያን ከድህነት ወለል በታች እንዲኖሩ ካደረጉ ዓበይት ምክንያቶች ዓለም አቀፍ አፅናፋዊ የምጣኔ ሃብት ትስስርንም ተጠቃሽ አድርጎታል። ይሁን እንጂ ምዕራባውያን መንግስታት፣ የዓለም ባንክና ዓለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ድርጅት በበኩላቸው አፍሪቃ በምጣኔ ሃብት እንድታድግ ገበያዎቿን መክፈትና ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላትን የንግድ ግኑኝነት ማስፋፋት እንዳለባት ያሳስባሉ።

የተለያዩ ገፅታዎች

በማዳመጥ መማር ክርክሩ ውስጥ አይገባም። ከዚህ ይልቅ ዝግጅቶቹ ዓለም አቀፍ የአፅናፋዊ የምጣኔ ሃብት ትስስር ያስከተላቸውን የተለያዩ ገፅታዎች ይቃኛሉ። ዘጋቢዎቻችን በዚህ ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለተሻለ ኑሮ በተለያዩ የአፍሪቃና አውሮጳ ከተሞች ከሚገኙ ሰዎች፤ እንዲሁም የተሻለ ኑሮ ካላቸው ስራ ፈጣሪ ሰዎች ጋ ይነጋገራሉ። በተጨማሪም ዝግጅቱ የአፍሪቃ ምጣኔ ሃብት የጀርባ አጥንት የሆነው ግብርና በዓለም አቀፍ የአፅናፋዊ የምጣኔ ሃብት ትስስር ምክንያት ምን ያህል እየተቀየረ እንዳለ ያሳያል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ይቀርባል። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ደግመው ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎን

www.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።

Audios and videos on the topic