አጠያያቂዉ የአቶም ኃይል ምንጭ | ጤና እና አካባቢ | DW | 05.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

አጠያያቂዉ የአቶም ኃይል ምንጭ

ለተለያዩ አገልግሎቶች ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣዉ የኤሌክቲሪክ ኃይል በልዩልዩ ስልቶች መመንጨት እንደሚቻል ዘመንና የቴክኒዎሎጂ እድገት እያስመሰከሩ ነዉ።

default

እንዲያም ሆኖ ኒኩሊየርን ለኃይል ምንጭነት የመጠቀሙ ስልት ከመነሻዉ ካለተቃዉሞ ከዚህ አልደረሰም። ከሰላሳ በላይ ሀገራት የኒኩሊየር ኃይል ተጠቃሚዎች መሆናቸዉን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሌሎች በርካቶችም በዚሁ መስመር ለመግባት እየጣሬ ነዉ። ያም ሆኖ የዛሬ 25ዓመት በቼርኖቤል የአቶም ኃይል ማመንጫ ተቋም የደረሰዉ ፍንዳታ ባስከተለዉ አደገኛ ጨረርና የኬሚካሎች ልቀት በርካቶች ለተለያየ የካንሰር በሽታ መጋለጣቸዉ ይታወቃል። የሰሞኑ የጃፓን ፉኩሺማ አራት የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫዎች ጉዳት በባህርና፤ በአካባቢዉ ብሎም በከባቢ አየር ላይ ችግር ማስከተሉ የብዙዎችን ስጋት ከፍ አድርጎታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሠ

ተዛማጅ ዘገባዎች