አዶት ዲዛይን ባህላዊ ቁሳቁስና አልባሳት | ባህል | DW | 23.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

አዶት ዲዛይን ባህላዊ ቁሳቁስና አልባሳት

«አባቴ ጫማ ሰራተኛ ስለነበር በልጅነቴ ሲሠራ አይነበር፤ አግዘዉም ስለነበር ብዜ ሞያን ከሱ ተምሪአለሁ» ትላለች፤ ከወፍቾ የተለያዩ ጌጣጌጦች፤ ቦርሳና ጫማ ከሸማ ዉጤት ከሆነዉ ከጥለት ጋር በመቀላቀል፤ ለተጠቃሚ እያቀረበች ታዋቂነትን ያገኘችዉ ወጣት ተሻለች ታደሰ፤ የ«አዶት ዲዛይን» ባለቤት።»

የኢትዮጵያ የባህል አልባሳትና ሌሎች የኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ምርቶችን በፋሽን ዘመናዊ ዕቅድ ልዩ መልክ በመሥጠትና ገበያ ተኮር በማድረግ በሃገር ዉስጥ ተወዳጅነቱ ይበልጥ እንዲጠነክር ብሎም በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ በማስተዋወቅ ላይ የሚገኙ ባለሞያዎች እየተበራከቱ መምጣታቸዉ ይነገራል። በዕለቱ ዝግጅታችን በወፍቾ የኢትዮጵያ ባህላዊ ቁሳቁሶችን የሚያመላክቱ ጌጣጌጦችን ቦርሳና ነጠላ ጫማን የሽመና ዉጤት ከሆነዉ ጥለት ጋር በማዋኃድ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች በማስተዋወቅዋ ታዋቂ ሥለሆነችዉ ወጣት ባለሞያና ሥራዎችዋን ይዘን ቀርበናል።

ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸዉ በርካታ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች መካከልየሕዝቦችዋ ባህላዊ አልባሳት፤ ጌጣጌጥና መገልገያ ቁሳቁሶችን ገበያ ተኮር በማድረግ ዓይን በሚስብ መልኩ ደማቅ መልክ በመሥጠት ተወዳጅነቱ እንዲጨምር እያደረገች መሆንዋ የሚነገርላት የ30 ዓመትዋ ወጣት ተሻለች ታደሰ፤ ምርቶችዋን የአፍሪቃ ሕብረትን ጨምሮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በሚበኙኑ የዉጭ ሃገር ድርጅቶች በማቅረብ ባህልዋን በማስተዋወቅዋ ብሎም ጥሩ ሥራ ፈጣሪ መሆንዋ ተገልፆላታል። የጅማ ዩንቨርስቲ የሶስዮሎጂ ትምህርት ምሩቅዋ ወጣትዋ የሸማና ሌሎች የኢትዮጵያ ባህላዊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ እዉቅናን ያገኘችዉ ወ/ት ተሻለች ታደሰ በቃጫ በኮባ ልጥ በወፍጮና በሸማ ጥለት ለገበያ የምታቀርባቸዉ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ቁሳቁሶች ጌጣጌጦች እንዲሁም ቦርሳና ጫማን ከመሥራትዋ በፊት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርም ነበረች። ይህን ባህላዊ ቁሳቁስ መሥራት የጀመርኩት ትላለች ወ/ት ታደለች፤ መጀመርያ እኔ አባቴ ጫማ ሠሪ ስለነበር ከዙ ጋር ብዙ የእጅ ሞያን በመማሪ ነዉ። በህጻንነቴ አባቴን በጫማ ስራዉ አግዘዉ ነበር። በወፍቾ ግን አንድን ነገር ለመሥራት የተነሳሁት እቤታችን እንሰት ይፋቅ ነበር፤ እናቴ እንሰት ትተክል ነበር። እንሰቱ አድጎና ተፍቆ እንበላ ነበር።

ወፍቾ ቃቻ ምርት ላይ ሲዉል አይ ነበር። ከዝያም ነዉ እንሰት ብዙ ጥቅም እንደሚሰጥ ተረድቼ ይህንን ስራ ለመጀመር የተነሳሳሁት»

የኢትዮጵያ የእድ ጥበብ ምርቶችንም ሆነ ሌሎች ባህላዊ ቁሳቁሶችን በዘመናዊ መልክ በማቅረብ በርካታ ወጣቶች ተሳታፊ ናቸዉ ሲሉ በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚ/ር የባህልና ኢንዱስትሪ ልማትና ትብብር ዳይሪክተር አቶ ደስታ ካሳ ገልፀዋል።

ምርቱ ባህላዊ ይዘቱን እንዳይለቅ ምን አይነት ጥረት ይደረጋል ለሚለዉ ጥያቄ በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚ/ር የባህልና ኢንዱስትሪ ልማትና ትብብር ዳይሪክተር አቶ ደስታ ካሳ እንደገለጹት» መሰረታዊ ባህሪዉን መልቀቅ የለበትም እንድያም ሆኖ ቅርጹ አልያም የልብስ ቅዱ ሊለዋወጥ ይችላል።

ምርቱ ገበያዉንና የተገልጋዩን ፍላጎት መሳብ ከቻለ፤ ዓለማቀፍ እና ባህላዊ ማለትም ሁለቱንም ባህርያቱን አንድላይ አጣጥሞ መያዝ መቻል አለበት ነዉ የሚባለዉ። ተጠቃሚ በሚመቸዉ መንገድ ልብሱ ሊሰፋ፤ አልያም መገልገያዉ ቁስ ሊሰራ ይችላል። በዚህ ሁኔታ ባህላዊ መሰረቱን ባልጣሰ ሁኔታ ከቀረበ፤ ባህሉ ጠፋ ሊባል የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር አይችልም » ሲሉ ተናግረዋል።

በወፍቾ የተለያዩ ቁሳቁሶችን እና ባህላዊ ጌጣጌጦችን በመሥራትዋ የምትታወቀዉ ወ/ት ተሻለች ታደሰ ፤ አሁን አሁን በተለይ ባህላዊ የአበሻ ቀሚስ ባህሉን በለቀቀ መልኩ ይሰራል የሚለዉን ትችት ትቀበላለች። « ባህሉን ለቁዋል ሲባል የሚሰጠዉን አንዳንድ አስተያየት እኔ በግሌ እቀበላለሉ። ለምሳሌ ጥልፍን በከዉች በመጣ ጨርቅ ላይ ሲታይ ማለት ነዉ።

እዚህ ላይ ባህላዊዉ ነገር ጥልፉ ብቻ ነዉ ጥልፉ ግን እንደ ባህሉ በሽመና ከጥጥ በተሰራዉ ጨርቅ ላይ ቢያርፍ ተመራfጭነት ይኖረዋል። ከዚህ ደግሞ ጥሩ ሰደርያ፤ ሱሪ ቀሚስ ካባ ሁሉ መስራት ይቻላል። በአንጻሩ ከዉጭ በመጣ ጨርቅ ላይ እየቸለፍን በሸጥን ቁጥር ፤ አንደኛ ድንቅ የሆነዉ የሽመና ባህላችን ይጠፋል። ሁለተኛ ጥበቡም ወግም አይኖረዉም።»

በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን በማበረታታት ሥራ ላይ የተሰማራውና ፕሮጀክቱን የሚያስፈጽመው ድርጅት (ካዊ) መስራችና ዳይሬክተር ወይዘሮ ንግስት ኃይሌ በበኩላቸዉ ድርጅታቸዉ እንዲህ ዓይነትን ሥራ የሚተገብሩትን አዲስ ሥራ ፈጣሪዎች ይደግፋል፤ ሲሉ ተናግረዋል። ይህን አይነቱን የኢትዮጵያን ባህላዊ አልባሳት ጌጣጌች እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶች በዓለም አቀፍ መድረክ ለመዉሰድ መጣር የሃገሪቱን ባህልም ማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንዳለዉ ወይዘሮ ንግስት ኃይሌ ገልፀዋል።

ሥራዬና ንግድ ላይ ድፍረትን እወዳለሁ ያለችን ወጣት ተሻለች ታደሰ፤ በወፍቾ ስለምትሰራቸዉ የተለያዩ ባህላዊ ጌጣጌጦች ቦርሳና ጫማ እና ስለባህላዊዉ የሽመና ዕደ ጥበብ ጉዳይ በሰፊዉ አጫዉታናለች ። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic