አድቬንት ክራንዝ ምንድን ነዉ | ባህል | DW | 29.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

አድቬንት ክራንዝ ምንድን ነዉ

በርካታ አዉሮጻዉያን አገራት የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ባለፉት ቀናት የገናን በአል በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል። እዚህ በጀርመን ከረቡዕ ምሽት ጀምሮ እስከ አርብ አለት ድረስ ገናን አክብረዋል።

አድቬንት ክራንዝ

አድቬንት ክራንዝ

ያ ማ ለት ረቡዕ ምሽት ጌታ የሚወለድበት እለት በነጋታዉ አንደኛዉ ገነና በአል ቀን ከዝያም ቀጥሎ ያለዉ ቀን ሁለተኛዉ የገና የበአል ቀን በማለት እያንዳንዱ ቤተሰብ ተሰባስቦ የልደትን በአል ያከብራል።በዛሪዉ ዝግጅታችን እዚህ በጀርመን የገና በአል ከመድረሱ በፊት ባሉት አራት ሳምንታት ዉስጥ አድቬንት እያሉ ስለሚጠሩት ማለት በየሳምንቱ እሁድ ሰለሚያስቡት ቀን እና ስለ አድቬንት ክራንዝ በጥቂቱ ልንላችሁ ተዘጋጅተናል

በጀርመን የገና በአል ከመድረሱ አራት ሳንት በፊት በመጀመርያዉ እሁድ አንድ ሻማ በሁለተኛዉ እሁድ ሁለተኛ ሻማ በሶስተኛዉ እሁድ ሶስተኛ ሻማ በአራተኛዉ እሁድ እንደዚሁ አራተኛ ሻማ ይበራና ከዝያም የጌታ መወለድ ይበሰራል በጀርመን የሚኖር ህጻን ይህን ጉዳይ ጠንቅቆ ያዉቃል። በተለይ በተለይ የገና በአል ሲደርስ ህጻናት የምኞታቸዉን የገና አባት ያመጣል ብሎ ስለሚያስቡ እና ህጻናት ስጦታቸዉን ጌታ የተወለደበት እለት ባሸበረቀዉ የገና ዛፍ ስር የገና አባት አስቀምጦ እንደሚሄድ ስለሚያዉቁት በጉጉት የሚጠብቁት እለትም ነዉ። ይህ ገና ከመድረሱ አራት ሳምንት በፊት የሚበራዉ አራት ሻማ የሚቀመጠዉ እንደቀለበት በተጎነጎነ የጥድ ዝንጣፊ ላይ ሲሆን ይህም አይነት ልማድ ለመጀመርያ ግዜ እዚህ በጀርመን እንደ አ. አ 1839 አ.ም እንደ ተጀመረ ይነገራል።