አዳጊው የፊልም ተዋናይ | ባህል | DW | 24.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

አዳጊው የፊልም ተዋናይ

ታዳጊ የፊልም ተዋናይ ነው። እዮብ ዳዊት። 23 ፊልሞችን ተውኗል። አዲስ በሚወጡ ፊልሞች ላይ እሱን ማየታችን አዲስ አይሆንም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 08:50

ኢዮብ ዳዊት የፊልም ተዋናይ

በፊልም ሥራዎች ላይ መተወን የጀመረው በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ላለፉት ሰባት ዓመታትም 23 ፊልሞችን ተውኗል። ያልታሰበው መጀመሪያ በትወና የተሳተፈበት ፊልም ነው፤ በዘጠኝ ዓመቱ። ብላቴና የሚለው ደግሞ ሁለተኛው። የ16 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት እዮብ ዳዊት። አጼ ማንዴላ፣ ደስ ሲል፣ የልጅ ሀብታም፣ እስክትመጪ ልበድ፣ ያልታሰበው፣ የአራዳ ልጅ ፣ ይመችሽ የአራዳ ልጅ 2፣ ያበደች የአራዳ ልጅ 3፣ ከተወነባቸው ፊልሞች ጥቂቶቹ ናቸው።  ከአዳጊው ወጣት የፊልም ተዋናይ እዮብ ዳዊት ጋር የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ። 

 

ነጃት ኢብራሂም 

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic