አዳማና ባንኮክ ሃኪም ቤቶች | ኢትዮጵያ | DW | 22.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አዳማና ባንኮክ ሃኪም ቤቶች

አቅማቸዉ የፈቀደላቸዉ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ህመምተኞች ዛሬ ጊዜ ለህክምና ወደታይላንድ ባንኮክ እንደሚሄዱ ይወራል።

default

ለተሻለ ህክምና ባህር ተሻግረዉ ከሚሄዱት መካከል ከመድሃኒቱ የተገናኙ የመኖራቸዉን ያህል ትርፉ ወጪ የሆነባቸዉም አልታጡም። ህመምተኞቹን ወደዚያ በመዉሰድ የሚያስተናግድ ድርጅትም አገር ዉስጥ አለ። ሰሞኑ ደግሞ የአዳማ ሃኪም ቤት ከባንኮክ ኢንተርናሽናል ሃኪም ቤት ጋ የስራ ትብብር ዉል ተፈራርሟል። ስምምነቱ ባለሙያዎችን ወስዶ ከማሰልጠን ባሻገር፤ የተወሳሰበ የጤና እክል ሲገጥም አገር ዉስጥ ያሉት ሃኪሞች ታይላንድ ካሉት ጋ በቀጥታ ተገናኝተዉ መፍትሄ ማፈላለግን ሁሉ እንደሚያካትት ተገልጿል።

ጌታቸዉ ተድላ

ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ