አዲስ የጥንታዊው ሰው ቅሪተ አካል በኢትዮጵያ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 11.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

አዲስ የጥንታዊው ሰው ቅሪተ አካል በኢትዮጵያ

ባለፈው ሳምንት፣ በዛሬዋ ዕለት ነበረ፣ የሳይንሱ ዓለም ፣ በተለይም የጥንታዊው ሰውም ሆነ ቅድመ ሰው ቅሪተ አካል ተመራማሪዎች ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ 2,8 ሚሊዮን ዓመት ገደማ ዕድሜ ያለው መንገጭላ ከ 5 ጥርስ ጋር መገኘቱን በይፋ በማሳወቅ ደስታቸውን

የገለጡት። ኢትዮጵያ ውስጥ በአፋር ምድር፤ ሌዲ-ገራሩ በተሰኘው የምርምር አካባቢ LD 350-1 የሚል ሳይንሳዊ መለያ ስም የተሰጠው ቅሪተ አካል፤ በጥቂት መቶ ሺ ዓመታት ልዩነት ቀደም ሲል ከተገኘችው ማለትም የ 3,2 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ካላት ይበልጥ ጦጣ መሰሏ ቅሪተ አካል Australopithecus afarensis ድንቅነሽ (ሉሲ) ይበልጥ ወደ ዘመናዊው ሰው ቅድመ ምስል ይጠጋል ነው የተባለው። ይኸው የመጀመሪያው የ Homo ቤተሰብ አባል ሳይሆን እንዳልቀረ የተነገረለትን ቅሪተ አካል፤ የዛሬው ዘመን ሰው (Homo Sapiens) እንዲሁም በሂደት የጠፉት ዘመዶቹ፣ Homo Habilis, Homo Erectus እና Neanderthals የጋራ የዘር ሐረግ ግንድ ሳያደርገው አልቀረም። በአፋር ምድር በተለያዩ ጊዜያት ፤ ከድንቅነሽ ሌላ ፤ ኢዳልቱ ፤ ሰላም የተባለችው ሴት ሕጻን ቅሪተ አካልና የመሳሰሉት መገኘታቸው የሚታወስ ነው። በሥነ- ቅሪተ አጽምም ሆነ ቅሪተ አካል ላይ ላተኮረው ምርምር ባለፈው ሰሞን ይፋ የተደረገው አዲስ የቅሪተ አፅም ጉዳይ የሚሰጠው ትርጉም ምን ይሆን? ---አቶ ዮናስ ደስታ

ስለሰው ፍጥረትና ዝግመታዊ ለውጥ ያተኮረው ሳይንስ እንደሚያስረዳው፤ የመጀመሪያዎቹ አንዳች ብልጥነት የማይታይባቸው ጦጣዎች ወይም ዝንጀሮዎች ከ 55 ሚሊዮንr ዓመatት በፊት በምድር ላይ ተከሠቱ ። ከ 15 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ከመለስተኛ ጦጣዎች ትልልቅ ጦጣዎች ብቅ አሉ።

ግዙፍ ዝንጅሮዎች (ጎሪላስ) ከ 8 ሚሊዮን ዓመት በፊት በተለይ የመጀመሪያዎቹ ጎሪላዎች፣ በገጽ ምድር ላይ መንጎራደድ የጀመሩበት ምዕራፍ ነበረ። ከዚያ በኋላ የጦጣዎችና የሰው የዘር ሐረግ እንደተለያየ ነው የሚነገረው። ከ 5,5 ሚሊዮን ዓመት በፊት፤ የጦጣዎችንና የጎሪላዎችን ባህርያት የሚጋራ «አርዲፒተከስ» ጥንተ Homo Sapiens ብቅ አለ። ከቺምፓንዚ(ጦጣ) የማይበልጥ የራስ ቅል የነበረው አውስትራሎፒተሲንስ የተባለው ደግሞ ከ 4 ሚሊዮን ዓመታት በፊት መከሠቱ ይነገርለታል። ከ 2,8 ሚሊዮን ዓመት በፊት ቀደም ሲል እንደተገለጸው፤ LD 350-1 ብቅ አለ ፣ በደፈናው ሰው የሚባለው የመጀመሪያ ቤተሰብ ለመሆን የበቃው ማለት ነው። ከ 2,7 ሚሊዮን ዓመት በፊት፣ ለመጎርደም ፣ለማላመጥ የሚጠቅም ትልቅ መንገጭላ የነበረው «ፓራንትሮፐስ» የተሰኘው ፍጡር ታየ። ከ 2,3 ሚሊዮን ዓመት በፊት ሆሞ ሃቢሊስ የተሰኘው በአፍሪቃ ምድር ተከሠተ። ሆሞ «ኤርጋስተር» የተባለው 1,8 ሚሊዮን ዓመታት ያስቆጠረ ታሪክ ያለው ነው። ከ 1,6 ሚሊዮን ዓመታት በፊት መጥረቢያ የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤት ሆነ። ከ 800,000 ዓመት በፊት የጥንት ሰዎች እሳትን ጥቅም ላይ ማዋል፤ መቆጣጠር ቻሉ። በራስ ቅል ውስጥ፣ የአንጎላቸው መጠንም በፍጥነት አደገ።

ከ 400,000 ዓመatት በፊት፤ «ኒያንደርታሎች» አውሮፓና እስያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሠት ብቻ ሳይሆን ተስፋፉ። ከ 200,000 ዓመታት በፊት ደግሞ፤ አስተዋዩ የሰው ፍጡር፣ በዛሬው አፍሪቃ ታየ። ከ 40,000 ዓመት በፊት የዘመኑ ሰው ተሠራጭቶ አውሮፓ ደረሰ።

ከቅድመ ሰው ፣ ወደ ዘመናዊው ሰው ለመምጣት የዝግመታዊው ለውጥ ምዕራፍ 6 ታይቶበት የነበረውን ክፍተት ነው እንግዲህ ፣ አሁን በአሪዞና ፌደራል ክፍለ ሀገር ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ትምህርቱን በመከታታል ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ወጣት ሳይንቲስት ቻላቸው መሥፍን ሥዩም ለመሙላት የበቃውና የሥነ ቅሪተ አጽም ተመራማሪውን ዓለም ያስደመመው። እርሱን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት በዚያው በአሪዞና ዩንቨርስቲ አገናኝ ክፍሎች ለትብብር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሳካልን አልቻለም ። ይሁንና ተመራማሪው ወጣት ምሁር ስላገኘው ቅሪተ-አፅምና ስለአንድምታው ---

ኢትዮጵያ ውስጥ ፣ የዘመናዊውን ሰው አመጣጥ ፣ ምዕራፍም ሆነ እርከን የሚያሳዩ የምርምር ውጤቶች በየጊዜው ተመዝግበዋል፤ስለተለያዩት ቅድመ ሰው ፍጡራን አኗኗር የሚጠቁሙ ተጨማሪ መረጃዎች ዋቢነት ምን ይመስላል?

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic