አዲስ የግንባታ ሕግ ለኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 30.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አዲስ የግንባታ ሕግ ለኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር «የግንባታ የጥራት ደረጃዎችን የሚቆጣጠር አስገዳጅ የግንባታ ሕግ» ማዘጋጀቱን የአገር ዉስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:35

የግንባታ ሕግ

በጥቅምት ወር ተፈፃሚ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀዉ ይህ አዲስ ሕግ በግንባታ ዘርፍ የሚታዩትን የግንባታ ጥራት መጓደሎች፣ የግንባታዎች ፍጥነት ማነስና ደረጃቸዉን ያልጠበቁ የግንባታ ግብዓቶችን የሚያሻሽል እንደሆነ ዘገባዉ ያሳያል።
በሚንስቴር መሥርያ ቤቱ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች መሳርያዎችና ባለሙያዎች ምዝገባና የብቃት ማረጋገጫ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ደስታ ሸዋሞላ ስለ አዲሱ ሕግ ይዘት በተመለከተ ለዶቼ ቬሌ እንገለፁት ሕጉ 14 ኮዶች አሉት።


በኮንስትራክሽን ሚኒስቴት በፊት የወጣዉ የኢትዮጵያ የሕንጻ ግንባታ ኮዶች ለረጅም ግዜ ስሰራበት የቆየ ስሆን አሁን በአዲስ መቀየር ያስፈለገበት ምክንያት የዘመኑን ቴክኖሎጂ ለማካትትና አዳዲስ ግኝቶችን መሠረት ያደረገ እንድሆን ታስቦ እንደሆን ወ/ሮ ደስታ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።


የዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ድረ ገፅ ተከታታዮች አዲስ ሕግ ስለተባለዉ ጉዳይ እንዲወያዩ እንዲሁም አስተያየት ጠይቀን ነበር። አንዳዶቹ መንግሥት ሕጉን ተፈፃሚ ሳያደርግ በፊት በዘርፉ ዉስጥ ካሉት ማኅበረሰብ ጋር ተወያይቶ ግልፅ ስምምነት ላይ መድረስ አለበት «ካልሆነ ቅሬታ ሊፈጠር ስለሚችል የራሱ የሆነ ዓሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል» ይላሉ። ሌሎች ደግሞ በግንባታ ጊዜ ሠራተኞች ላይ ከከባድ እስከ ቀላል አደጋ ይደርስባቸዋል ግን አደጋ የደረሰባቸዉ ሰዎች እንክብካቤ እና ሕክምና ሲደረግላቸዉ አናይም ስለዚህ መንግስት የኮንስትራክሽን ፍቃድ ሲሰጥ መሟላት ያለበት አንደኛው ነገር ሠራተኞች ሕክምና እንዲገኙ ማደረግ አለበት ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዉልና።


መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic