አዲስ የስደተኞች መጠላያ ጣቢያ በባየር | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አዲስ የስደተኞች መጠላያ ጣቢያ በባየር

አዲስ በተከፈተዉ ማዕከል ከደቡባዊ አዉሮጳ የመጡ 500 ያህል ስደተኞች እንደሚኖሩበት ተመልክቶአል። በማዕከሉ ከሚጠለሉት ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ በዘላቂነት ጀርመን ዉስጥ የመኖያ ፈቃድ የማያገኙ መሆናቸዉ ተመልክቶአል

በጀርመን ባየር ግዛት የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሚሊያ ሙለር ከምዕራብ ባልካን ሃገራት ለሚመጡ ስደተኞች በጀርመን የመጀመርያና ልዩ የሆነ የስደተኞች መጠለያ ማዕከል መከፈቱን ገለፁ። ባየር ግዛት «ኢንጎልሽታድት» በተሰኘ ከተማ የተከፈተዉ ይህ የስደተኞች መጠለያ ማዕከል በቀድሞ ጊዜ ትልቅ የወታደሮች ሠፈር እንደነበረም ታዉቋል። አዲስ በተከፈተዉ ማዕከል ከደቡባ አዉሮጳ የመጡ 500 ያህል ስደተኞች እንደሚኖሩበት ተመልክቶአል። በማዕከሉ ከሚጠለሉት ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ በዘላቂነት ጀርመን ዉስጥ የመኖ ፈቃድ የማያገኙ መሆናቸዉ ተመልክቶአል።እንደ በራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤሚሊያ ሙለር የስደተኞቹን ጉዳይ የሚያዩ ባለሥልጣን መስርያ ቤቶች በቅርርብ በመሥራት የተገን ጠያቂዎችን ጉዳይ ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በማጣራት ፈቃድ ያላገኙ ተገን ጠያቂዎች ወደ ሃገራቸዉ እንዲላኩ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ