አዲስ ዓመትና ኢትዮጵያውያን በአውሮጳ | ባህል | DW | 02.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

አዲስ ዓመትና ኢትዮጵያውያን በአውሮጳ

የጎርጎሪዮሳዊውን የቀን ቀመር ለሚያሰሉ አዲስ ዓመት ማለትም 2014 ከጠባ ዛሬ ማግስቱ ነው። የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ አቀባበልን በአውሮጳ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን እንዴት ይመለከቱታል? ከዝግጅቱ የምናገኘው ይሆናል።


በጎርጎሪዮሳዊው የቀን ቀመር ስሌት መሰረት አሮጌው ዓመት ተሰናብቶ አዲሱ 2014 ዓመት ከባተ ዛሬ ማግስቱ ላይ ነው የምንገኘው። «አዲስ ዓመትና ኢትዮጵያውያን በአውሮጳ» የዝግጅታችን ርዕስ ነው። ዓለማችን የተለያየ የቀን ቀመርን የምትከተል የመሆኗን ያህል በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ ፅንፍነት ብቻ አንድ አይነት የቀን አቆጣጠር ቀመር ውስጥ የሚገኙ ሃገራት እንኳ አዲስ ዓመትን ከግማሽ ቀን በበለጠ ልዩነት ነው ተቀዳድመው የሚያከብሩት። የገና ደሴት የምትሰኘው የአውስትራሊያ ግዛትን እና ሳሞዋ የምትባለው ሌላኛዋ ደሴትን ቀዳሚ ያደረገው የአዲስ ዓመት ብስራት አውሮጳ ሲደርስ አቀባበሉ ምን ይመስል ነበር፤ በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ?

በነገራችን ላይ አዲስ ዓመትን ካነሳን አይቀር፤ ከዓለማችን ቀድመው አዲስ ዓመትን የሚቀበሉት ሳሞዋና የገና ደሴት የሚባሉ በህንድ ውቅያኖስ ላይ ተነጥፈው የሚገኙ ደሴቶች ናቸው። ከዛሬ ሶስት ዓመታት በፊት 1500 ያልሞላ ነዋሪ የነበራት የገና ደሴት በመልክዓ-ምድር አቀማመጧ ህንድ ውቅያኖስ ላይ ተዘርግታ ብትገኝም በፖለቲካ ግን የአውስትራሊያ ግዛት ናት። እጎአ በ1962 ከኒውዚላንድ ተነጥላ ነፃነቷን ያወጀችው ሳሞዋ ደሴት እና የአውስትራሊያዋ የገና ደሴት አዲስ ዓመትን እዚህ ጀርመን ሀገር ከመቀበላችን 13 ሠዓታት ግድም ቀድም ብለው ነው ያከበሩት። ባከርና ሆውላንድ የተሰኙት የዩናይትድ ስቴትስ ደሴቶች ደግሞ አዲስ ዓመትን ከነሳሞዋ ደሴቶች አንድ ቀን ዘግይተው ገና ትናንት እኩለ-ቀን ላይ በመቀበል የመጨረሻዎቹ ሆነዋል። የዓለም መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ አንዱ ጋ ቀድሞ ሲነጋ ሌላው ጋ የመምሸቱ ምስጢር መሆኑ ነው።

ሙሉ ዝግጅቱን ለማድመጥ ከታች ያለውን የድምፅ ማጫወቻ ይጫኑ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic