አዲስ አበባ፤ የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ኅብረት ትብብር ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 07.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አዲስ አበባ፤ የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ኅብረት ትብብር ጉባኤ

የአፍሪቃ ኅብረት እና የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን የጋራ ትብብር ጉባኤ ተካሄደ። ሁለቱ አህጉሮች በተለይም በስደተኞች፤ በሰላም እና በፀጥታ እንዲሁም በዘላቂ እድገት ላይ ያተኮረ ዉይይት እንዳካሄዱ ተጠቅሷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:16
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:16 ደቂቃ

አፍሪቃእ እና የአውሮፓ

የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ኅብረት ከ9 ዓመታት በፊት ሊዝበን ላይ ባካሄዱት ጉባኤ ለትብብራቸዉ የጋራ ስልት ቀይሰዉ አጽደቀዋል። በየዓመቱ በሚያካሂዱት ስብሰባም በተለይ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2014 እስከ 2017 ዓ,ም የቀየሱትን ስልት በአምሥት ዘርፎች ማለትም በሰላም በጸጥታ፤ በዴሞክራሲ፤ እንዲሁም መልካም አስተዳደር እና ሰብዓዊ መብቶችን በተመለከተ በዉይይት እና ትብብር ተግባራዊ ለማድረግ አቅደዋል። በጉባኤዉ ላይ የተገኙት የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ፌዴሪካ ሙገሪኒ የኅብረቱ እና የአፍሪቃ ትብብር እና ዉይይት ስደተኞችን ከመከላከል የዘለለ መሆኑን አመልክተዋል።

«የስደት ጉዳይ አንደኛዉና ቁልፍ የትብብራችን ዘርፍ ነዉ። ሆኖም ግን ብቸኛዉ እና እጅግ አስፈላጊዉ እንዳልሆነ ግን በግልፅ አፅንኦት መስጠት እፈልጋለሁ። ምክንያቱም በዛሬዉ ጉባኤ መጀመሪያ ላይ አብዛኞቻችን እንደገለጽነዉ የትብብራችን አቅጣጫ ብዙ እና ከኤኮኖሚዉ ጉዳይ እና ከሥራ መስክ ፈጠራዉ አንስቶ ሁሉም ጠቃሚዎች ናቸዉ።»

Afrikanische Union Flaggen

የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮችና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ፌደሪካ ሞጎሮኒ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የአውሮጳ ህብረት ከ13 የአፍሪቃ ሃገሮች ጋር በስደተኞች ጉዳይ ላይ አብሮ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሷል ።

የአፍሪቃ ኅብረትና የአውሮጳ ኅብረት በጋራ በሚሰሩባቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ አካሄዱ ። ዛሬ ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከል ባለፈው ዓመት የተጀመረው ሁለቱ ወገኖች በሰደተኞች ጉዳይ ላይ በጋራ የሚያከናውኑት ተግባር ይገኝበታል ። የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮችና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ፌደሪካ ሞጎሮኒ ዛሬ አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የአውሮጳ ኅብረት ከ13 የአፍሪቃ ሃገሮች ጋር በስደተኞች ጉዳይ ላይ አብሮ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሷል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic