አዲስ አበባ፥ በእጅ ቦንብ 2 ተማሪዎች ተገደሉ | ኢትዮጵያ | DW | 01.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አዲስ አበባ፥ በእጅ ቦንብ 2 ተማሪዎች ተገደሉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተጣለ የእጅ ቦምብ ሁለት ተማሪዎች መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ ። በፍንዳታው ስድስት ተማሪዎች መቁሰላቸውንም የዜና ምንጩ ሮይተር ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ በጥቃት ፈጻሚው አለያም ፈጻሚዎቹ ቦምቡ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተጣለው ሐሙስ ምሽት ላይ ነው።

ፖሊስ ለጥቃቱ መንስዔ ማብራሪያ አልሰጠም ሲል የሮይተርስ ዘገባ ገልጧል። «ፍንዳታው ሁለት ተማሪዎችን ገድሏል፤ ስድስት አቁስሏል። ከቆሰሉት መካከል የአራቱ ጽኑዕ ነው።» ሲሉ የከተማዋ ፖሊስ ባልደረባ እጅጉ ሽፈራው መንግሥታዊ ለሆነው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ከጥቃቱ በኋላ ቁጥራቸው በውል ያልተነገረ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል። ባሥልጣናት ስለ ጥቃቱ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም ያለው የሮይተርስ ዘገባ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩንም ገልጧል። ዘገባው ከአዲስ አበባ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዲላ ይኽ ነው የተባለ አለመረጋጋት በቅርብ ዘገባዎች አልታዩም ነበር ሲልም አክሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት ጥቃት ሲፈጸም በሦስት ሣምንታት ጊዜያት ሁለተኛው እንደሆነ ፖሊስ ተናግሯል። ከ 21 ቀናት በፊት በአዲስ አበባው የአንዋር መስጊድ ቦምብ ፈንድቶ ከ20 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ይታወሳል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ


ተዛማጅ ዘገባዎች