አዲስ አመት እና ኢትዮጽያዉያን | ባህል | DW | 15.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

አዲስ አመት እና ኢትዮጽያዉያን

የክረምቱ ጭጋግ እና ብርድ አልፎ፣ አሮጌ ዘመን ሄዶ አዲስ ዘመን ተተክቶአል፣ በመስከረም ስፍራዉ ሁሉ ለምለም፣ እዮሃ አበባዪ ብለናል! የጨለማ ተምሳሌት የሆነዉ የክረምቱ ወራት አልፎ መስከረም ሲጠባ፣ ጎረቤት ቤት፣ ዘመድ፣ የአገር ሰዉ በባህላችን እንኳን ከጨለማ ወደ ብርሃን አሸጋገራችሁ!

default

በሸዋ በትግሪ በጎንደር በጅማም ያላችሁ፣ እንዴት ከረማችሁ! ይባላል። አዲስ አመትን ለመቀበል ቤት ልብስ አጠባዉ፣ ጉዝጓዙ፣ ጠላዉ፣ ዶሮዉ፣ ዳቦዉ፣ በየማህበረሰቡ፣ በየቤቱ፣ የእንቁጣጣሽ የዘመን መቀየርያ ዝግጅቱ የተለያየ ነዉ። በአዲስ ዘመን መግብያ ህጻናት እና ልጃገረዶች አደይ አበባ እንግጫ እየለቀሙ እና እየጎነሆኑ ሲቦርቁ እረኛ የሚያግዳቸዉ ከብቶች እንኳ አምልጠዉ አዝመራ ቢበሉ እንደሌላዉ ግዜ እረኛዉ ቁጣ አደርስበትም! ከብቶችም በአዲስ አመት አተላ ባያገኙ ከዝመራዉ ጠጋ ማለት አይከለከሉም አሉ! በአዲስ አበባ ቢሆን አዲስ አመትን ለመቀበል፣ በመባቻዉ ልብስ አጠባዉ፣ ቤት ጠረጋዉ አላስፈላጊን ነገር አብሮ ከአሮጌዉ ጋር ለመሸኘት እሽቅድምድም የተያዘ ይመስላል። ብቻ ብዙ ግዜ ዉሃ መጥፋትዋ ስለማይቀር፣ ወዲህም የጳጉሜም ዉሃ ጥሩ ነዉ በመባሉ፣ የዝናብም ሆነ የቧንቧ ዉሃ አዲስ አመት ከመድረሱ በፊት በጉርድ በርሜል ማጠራቀሙ የማይቀር ነበር። በአዲስ አመት ሲብት ደግሞ በጥዋት በባዶ ሆድ የፊጦ ፍትፍቱ እና ገላ መታጠቡ ባደኩበት በአዲስ አበባ ለመኖሩ መስካሪ ነኝ። በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የፎልክሎር ትምህርት አስተማሪ የሆኑት መምህር መስፍን መሰለ፣ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ታደለ ገድሌ እንዲሁም በበርሊን የአማኑኤል ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ ስለአዲስ አመት አቀባብል ባህል የሚያዉቁትን ያዩትን ያጫዉቱናል ሙሉዉን ጥንቅር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic