አዲስ ተመራጮቹ የአዉሮጳ ኅብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 31.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

አዲስ ተመራጮቹ የአዉሮጳ ኅብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት

የ28ንቱ የአዉሮጳ ሃገራት መንግሥታትና ጠቅላይ ሚኒስትሮች፤ ትናንት ብራስል ላይ ልዩ ጉባኤ ካካሄዱ በኋላ ለኅብረቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሄርማን ቫን ሮምፑይ እና ለኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃለፊ ካትሪን አሽተን ፤ ተተኪ መረጡ።

የኅብረቱ አባል ሀገራት፤ መንግሥታትና የመንግሥት ተወካዮች በዉሳኔአቸዉ፤ ለኅብረቱ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት፤ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ፤ ለኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃለፊ ደግሞ የኢጣልያዋ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊድሪካ ሞገሪንን መርጠዋል።
የ28ንቱ የአዉሮጳ ሃገራት መንግሥታትና ጠቅላይ ሚኒስትሮች፤ ትናንት ብራስል ላይ ባካሄዱት ልዩ ጉባኤ፤ እየተቀጣጠለ የመጣዉ የዩክሬይን ቀዉስ ዋና ርዕሳቸዉም ነበር። የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሆሴ ማኑኤል ባሮሶ ብራስል ላይ የዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ተቀብለዉ ባነጋገሩበት ወቅት፤ «ወደ ኋላ ልንመልሰዉ የማንችልበት ደረጃ ላይ ልንደርስ እንችላለን» ሲሉ ተደምጠዋል። የ28ቱ የአዉሮጳ ኅብረት መንግሥታትና የመንግስታት ተጠሪዎች ዛሬ ብራስል ላይ ለአንድ ልዩ ጉባኤ ተገናኝተዉ ነበር። ሩስያ በዩክሬይኑ ቀዉስ ላይ እጅዋ እንዳለበት የሚያመላክት በርካታ ነገሮች በመታየታቸዉ፤ ምናልባትም ኅብረቱ ሩስያ ላይ ከፍተኛ ማዕቀብ ለመጣል ሳይስማማ እንዳልቀረ ተዘግቦአል። በዛሬዉ የኅብረቱ ልዩ ጉባኤ፤ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሄርማን ቫን ሮምፑይ እና የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃለፊ ካትሪን አሽተንን የሚተካ ሰው እንደተፈለገም ተጠቅሶአል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ